የሓዲሦች ዝርዝር

ሲሸጥም፣ ሲገዛም ይሁን ያበደረውን ሲያስመልስ ገር የሆነን ሰው አሏህ ይዘንለት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በአላህ ገንዘብ ያለአግባብ የሚገለገሉ ሰዎች ለነርሱ የትንሳኤ ቀን እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ እንዲህ ብሏል: ‹ሁሉም የአደም ልጅ ስራ ለርሱ ነው ፆም ሲቀር፤ ፆም ለኔ ነው። በርሱ የምመነዳውም እኔው ነኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
(ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ጀነት ውስጥ ረያን የሚባል በር አለ። የትንሳኤ ቀን ጾመኞች በርሱ በኩል ይገባሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ረመዳን የገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የእሳት በሮችም ይዘጋሉ፤ ሰይጣኖችም ይጠፈነጋሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይሙላ። ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ህይወታቸውን እስከወሰደባት ጊዜ ድረስ የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶችን ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር። ከዚያም ከርሳቸው ህልፈት በኋላ ባለቤቶቻቸው ኢዕቲካፍ አድርገዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሌላ ጊዜያት ለአምልኮ ከሚጥሩት የተለየ በመጨረሻዎቹ አስሩ የረመዷን ቀናት ይጥሩ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ሌሊቱን ህያው ሆነው ያሳልፋሉ፤ ቤተሰባቸውንም ያነቃሉ፤ ይበረቱና ሽርጣቸውንም ያጠብቁ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን የጾመ ሰው አላህ ፊቱን ከእሳት ሰባ ዓመታት ያርቀዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ፍፁም ወዳጄ የሆኑት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ነገሮች ላይ አደራ ብለውኛል። ከሁሉም ወር ሶስት ቀናት በመጾም፣ የዱሓን ሁለት ረከዓ በመስገድና ከመተኛቴ በፊት ዊትር በመስገድ አደራ ብለውኛል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሰሑር ተመገቡ! በሰሑር ውስጥ በረከት አለ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ዒድን ከዑመር ቢን ኸጧብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ጋር ለመስገድ ተገኘሁ። እንዲህም አሉ: "እነዚህ ሁለት ቀናቶች የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመጾም የከለከሉት ቀናቶች ናቸው። (እነርሱም) ከጾማችሁ የምትፈቱበት ቀን (ዒድ አልፊጥር) እና ሌላኛው ቀን ደግሞ ከእርዳችሁ የምትበሉበት የሆነው ቀን (ዒደል አድሓ) ናቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ግንኙነትና ፆታዊ ስሜትን የሚያነሳሱን ሳይፈፅምና ሳያምፅ ለአሏህ ሐጅ አድርጎ የተመለሰ ልክ እናቱ እንደወለደችው ቀን (ከወንጀል ንፁህ) ሆኖ ይመለሳል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሐጅና ዑምራን አከታትላችሁ አድርጉ። ወናፍ የብረትን፣ የወርቅንና የብርን ቆሻሻ እንደሚያስወግደው እነርሱም ድህነትንና ወንጀልን ያስወግዳሉ። ተቀባይነት ላለው ሐጅ ከጀነት በቀር ሌላ ምንም ምንዳ የለውም።
عربي እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ተልቢያቸው "ለበይከ አልላሁምመ ለበይክ፣ ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ፣ ኢነልሐምደ ወንኒዕመተ ለከ ወልሙልክ ላ ሸሪከ ለክ" (አላህ ሆይ! ደግሜ ደጋግሜ ለጥሪህ አቤት እላለሁ፤ ምንም ተጋሪ የለህም። ምስጋና ፀጋና ንግስና ለአንተ ብቻ ነው፤ ምንም ተጋሪ የለህም።) የሚል ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'ከነዚህ ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራዎች ወደ አላህ ተወዳጅ የሚሆኑበት ምንም ቀን የለም።' ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ናቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አጋርያንን በገንዘባችሁ፣ በነፍሳችሁና በምላሳችሁ ታገሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
‹የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት እርጋታን የተላበሰ ነው። ውሸት ደሞ ጥርጣሬን የተላበሰ ነው።›
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ ከኡመቴ በውስጣቸው የሚናገሩትን ነገር እስካልሰሩት ወይም እስካልተናገሩት ድረስ ይቅር ብሏቸዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
‹አላህ ይቀናል። አማኝ የሆነ ሰውም ይቀናል። የአላህ መቅናት ሰውዬው አላህ በሱ ላይ ክልክል ያደረገበትን ሲዳፈር ነው።›
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ትላልቅ ወንጀሎች፦ በአላህ ማጋራት፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፣ ነፍስ ማጥፋትና የውሸት መሀላ ናቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የትንሳኤ ቀን በሰዎች መካከል መጀመሪያ የሚፈረደው ጉዳይ የደም ጉዳይ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኋላ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ላደረጉለት መልካም ነገር ምላሹን የሚሰጥ የሆነው አይደለም፤ ይልቁንም ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ዝምድናው በተቆረጠ ጊዜ የሚቀጥል የሆነው ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጎ ላደርግለት እጅግ የተገባው ማን ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም አባትህ ከዚያም ቅርብ የሆኑ ዘመዶችህ" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አስካሪ ሁሉ ኸምር ነው። አስካሪ ሁሉ ክልክል ነው። በዚህ ዓለም አስካሪ መጠጥ አዘውትሮ ጠጥቶ ንስሀ ሳይገባ የሞተ ሰው በመጪው ዓለም አይጠጣም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ ጉቦ ሰጪንም ተቀባይንም ረገሙ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አትመቀኛኙ፤ (ገዢን ለመጉዳት) አትጫረቱ፤ አትጠላሉ፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! የአላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነገር አዋሳጅ ጀነት አይገባም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'ወንጀላቸውን ይፋ ከሚያደርጉ በስተቀር ሁሉም ህዝቦቼ ይማርላቸዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ ከናንተ ላይ የድንቁርና ዘመንን ኩራትና በአባቶች መኮፈስን አስወግዷል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከሰዎች ሁሉ አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላው ደረቅ ተከራካሪ የሆነ ሰው ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሁለት ሙስሊሞች በሰይፋቸው (ሊጋደሉ) የተገናኙ ጊዜ ገዳዩም ሆነ ተገዳዩ እሳት ውስጥ ናቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
መሳሪያውን በኛ ላይ ያነሳ ከኛ አይደለም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ለአንድ ሰው ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ሲገናኙ ይህም ይዞራል ያኛውም ይዞራል። ከሁለቱ ምርጡ ሰላምታ የሚጀምረው ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በሁለት መንገጭላዎቹ መካከል እና በሁለት እግሮቹ መካከል ያሉትን አካላት (ሊጠብቅ) ዋስትና ለገባልኝ እኔም ጀነትን ዋስትና እገባለታለሁ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'ሴት ልጅ ከርሷ ጋር ባሏ ወይም ዘመዷ ከሌሉ በቀር ሁለት ቀን የሚያስኬድ መንገድን አትጓዝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከኔ በኋላ ለወንዶች ከሴት የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተና አልተውኩም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የጋብቻን ጣጣ የቻለ ሰው ያግባ! ጋብቻ አይንን ሰባሪና ብልትን ጠባቂ ነውና። ጋብቻን ያልቻለ ሰው መፆም አለበት። ፆም ለርሱ ማኮላሺያ (የጾታዊ ፍላጎቱን የሚቆርጥለት) ነውና።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ (ለምለም) ናት። አላህም እንዴት እንደምትሰሩ ሊያያችሁ በውስጧ ምትኮች አድርጓችኋል። ዱንያንም ተጠንቀቁ! ሴቶችንም ተጠንቀቁ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሚስታችን እኛ ላይ ያላት ሐቅ ምንድን ነው? አልኩኝ። እርሳቸውም "ስትበላ ልታበላት፤ የለበስክ ወይም የሰራህ ጊዜ ልታለብሳት፤ ፊቷን ላትመታ፤ ላታጥላላት፤ ከቤት ውጪ ባለ ቦታ ላታኮርፋት ነው።" በማለት መለሱልኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እናንተ የሴቶች ስብስቦች ሆይ! ምጽዋት ስጡ! እኔ አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች ሆናችሁ አይቻችኋለሁ።" ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በምን ምክንያት?" አሉ። እርሳቸውም "እርግማን ታበዛላችሁ፤ አኗኗሪን ትክዳላችሁ። አይምሮና ዲናቸው የጎደለ ሆኖ፤ ቆራጥ የሆነን ወንድ ልጅ ልብ የሚወስድም እንደናንተ አልተመለከትኩም!" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሴቶች ጋር ከመግባት ተጠንቀቁ!" አንድ ከአንሷር የሆነ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለባል ቅርብ ዘመዶች ንገሩኝ እስኪ?" አለ። እርሳቸውም "የባል ቅርብ ዘመድማ ሞት ነው።" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ያለ ወሊይ ፈቃድ ጋብቻ የለም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከወሊዩዋ (አሳዳጊዋ) ፈቃድ ውጪ ያገባች ማንኛዋም ሴት ጋባቻዋ ውድቅ ነው። (ንግግራቸውን ሶስት ጊዜ ደጋግሙት) እርሷን ከተገናኘም በመንካቱ ምክንያት መህሯ የራሷ ነው። ወሊዮች ከተጨቃጨቁም ወሊይ ለሌለው ሰው የሙስሊሞች መሪ ወሊዩ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሚስቱን በመቀመጫዋ የተገናኛት ሰው የተረገመ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'ልታሟሉት ከሚገቡ መስፈርቶች ሁሉ ልታሟሉት እጅግ የተገባው ብልትን ሐላል ያደረጋቹበትን መስፈርት ነው።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ዱንያ መጣቀሚያ ናት። ከዱንያ መጣቀሚያዎች ምርጡ መልካም ሚስት ናት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለድንገተኛ እይታ ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም አይኔን እንዳዞር አዘዙኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኡዱሒያ ሁለት ቡራቡሬና ቀንዳም የሆኑ ሙክቶችን በእጃቸው አረዱ። "ቢስሚላህ አላሁ አክበር" አሉና እግራቸውን አንገቱ ላይ አድርገው አረዱት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የሙስሊም ሽርጥ እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ ነው። ከባቱ ግማሽና በቁርጭምጭሚቱ መሃል ቢሆንም ግን ችግር የለውም። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ያለ ከሆነ እርሱ እሳት ውስጥ ነው። ሽርጡን በኩራት የጎተተን ሰው አላህ ወደርሱ አይመለከትም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የቀጭን ሐርንና የወፍራም ሐርን ልብስ አትልበሱ! በወርቅና ብር እቃ አትጠጡ! በ(ወርቅና ብር) ትሪም አትብሉ! እርሷ በዚህ ዓለም ለነርሱ ናት፤ በመጪው ዓለም ደግሞ ለኛ ናት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከሶስት ዓይነት አካላት ላይ ብእር ተነስቷል። የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ፤ ህፃን ልጅ አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ እና እብድ ጤነኛ እስኪሆን ድረስ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከልክለዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
መሃላ ሸቀጥን ተፈላጊ የሚያደርግ (የሚያዋድድ)፤ ትርፍን (በረከት) ደግሞ የሚያጠፋ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለውን ፂም) አሳጥሩ ሪዛችሁን (የመንጋጭላ ፂማችሁን) ልቀቁ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአብዛኛው ሰዎችን ጀነት ስለሚያስገባው ነገር ተጠየቁ፤ እሳቸውም "አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ነው።" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች ባጠቃላይ ይበልጥ ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ ሰው ነበሩ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ስነምግባር ቁርአን ነበር።' አለችኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጫማ ሲለብሱ፣ ሲያበጥሩ፣ ሲፅዳዱና በሁሉም ጉዳያቸው ቀኝን መጠቀም ይወዱ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አውቆ መጉዳትም ሆነ ሳያውቁ መጎዳዳትም የለም (አይቻልም)። ጎጂን አላህ ይጎዳዋል። ሰዎችን ያስጨነቀ አላህ ያጨናንቀዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አትቆጣ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አራት ነገሮች ያሉበት ሰው ጥርት ያለ ሙናፊቅ ይሆናል። ከነርሱ መካከል ከፊሉ ያለበት ሰው እስኪተወው ድረስ ከፊል ንፍቅና ይኖርበታል። ሲያወራ ይዋሻል፣ ቃልኪዳን ይዞ ያፈርሳል፣ ቀጠሮ ይዞ ያፈርሳል፣ ሲሟገት (ድንበር ያልፋል) በጥመት ላይ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሙእሚን የሆነ ሰው እጅግ ተቺ፣ እጅግ ተራጋሚ፣ ፀያፍ ተግባር ሰሪ፣ መጥፎ ንግግር ተናጋሪ አይደለም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አይነአፋርነት ከኢማን ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
መልካም ነገሮች ሁሉ ምፅዋት ናቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሁሉም የሰው ልጅ መገጣጠሚያ አጥንቶች ምፅዋት አለባቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
‹ባሏ ለሞተባትና ለሚስኪን የሚለፋ ሰው ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ሰው አምሳያ ወይም ልክ ሌሊት እየሰገደ ቀኑን እንደሚፆም አምሳያ ነው›
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ለሰዎች የማይራራን አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ አይራራለትም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ላይ አምስት መብቶች አሉት፤ ሰላምታ መመለስ፣ ህመምተኛ መጠየቅ፣ ጀናዛን መሸኘት፣ ጥሪውን መቀበልና ባስነጠሰው ጊዜ 'የርሐሙከሏህ' ማለት ናቸው።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'እስክታምኑ ድረስ ጀነት አትገቡም። እስክትዋደዱ ድረስም አታምኑም። የፈፀማችሁት ጊዜ የምትዋደዱበትን አንዳች ነገር ልጠቁማችሁን? በመካከላችሁ ሰላምታን አሰራጩ።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን?
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በሁሉም ውስጥ መልካም ነገር ቢኖርም፤ ጠንካራ ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን አላህ ዘንድ የተሻለና ይበልጥ ተወዳጅ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሚዛናዊ ሁኑ፤ በተቻለ መጠን ወደ እሱ ቅርብ ለመሆን ሞክሩ ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው እንደማይድንም እወቁ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሶም ቢሆኑ በስራዎት አይድኑምን?" አሉ። እርሳቸውም "አላህ ከርሱ በሆነ እዝነትና ችሮታ ካልሸፈነኝ በቀር እኔም ብሆን በስራዬ አልድንም።" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
(ጎረቤቴን) ያስወርሰዋል ብዬ እስከማስብ ድረስ ጂብሪል በጎረቤት (ሐቅ ዙሪያ) እኔን ከማዘዝ አልተወገደም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በአንድ ነገር ውስጥ ገራገርነት (ልስላሴ) አይኖርም ያስዋበው ቢሆን እንጂ ፤ ከአንድ ነገር ውስጥ ደግሞ አይነሳም አስቀያሚ የሚያደርገው ቢሆን እንጂ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የእስልምና ሃይማኖት ገር ነው። አንድም ሰው የእስልምናን ሃይማኖት ከመጠን በላይ አያጠብቅም (ሃይማኖቱ) የሚያሸንፈው ቢሆን እንጂ፤ ሚዛናዊ ሁኑ! አቀራርቡ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አግራሩ አታክብዱ! አበስሩ አታሽሹ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ዑመር ዘንድ ነበርንና እንዲህ አሉ: 'ከአቅም በላይ ከመጣጣር ተከልክለናል።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ የበላ ጊዜ በቀኙ ይብላ። የጠጣም ጊዜ በቀኙ ይጠጣ። ሰይጣን የሚበላውም በግራው፤ የሚጠጣውም በግራው ነውና።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንተ ልጅ ሆይ! ቢስሚላህ በል! በቀኝህ ብላ፣ ፊትህ ካለውም ብላ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'አላህ ባሪያው ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው ወይም መጠጥን ጠጥቶ እንዲያመሰግነው ይወዳል።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ሰውዬ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በግራ እጁ በላ። እርሳቸውም 'በቀኝህ ብላ።' አሉት። እርሱም 'አልችልም!' አላቸው። እርሳቸውም 'አያስችልህ!' አሉት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት የበላ ሰው ከኛ ገለል ይበል ወይም ከመስጂዳችን ገለል ይበል። ቤቱም ይቀመጥ" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ምግብ በልቶ ‹አልሐምዱ ሊላሂለዚ አጥዐመኒ ሀዛ ወረዘቀኒሂ ሚን ገይሪ ሐውሊን ሚንኒ ወላቁውዋህ› ያለ ሰው ያሳለፈው ወንጀል ለርሱ ይማርለታል።"» ትርጉሙም "ያለኔ ኃይልና ብልሃት ይህንን ላበላኝና ለለገሰኝ አላህ ምስጋና የተገባው ነው።" ማለት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ ግዴታ ያደረገው ሲተገበር እንደሚወደው፤ ያግራራውም ሲተገበር ይወዳል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ ለርሱ መልካም የሻለትን ሰው ይፈትነዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድን ሙስሊም ድካም፣ በሽታ፣ ሀሳብ፣ ሀዘን፣ ጉዳት፣ ጭንቀት የምትወጋው አንዲት እሾክ እንኳ (በከንቱ) አታገኘውም አላህ በሷ ምክንያት ከወንጀሎቹ የሚምርለት ቢሆን እንጂ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አማኝ የሆነ ወንድና ሴት በርሱ ላይ ምንም ወንጀል የሌለበት ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስ በነፍሱ፣ በልጁና በገንዘቡ ላይ መከራ ከመከሰት አይወገድም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአማኝ ነገር ይደንቃል። ሁሉ ነገሩ መልካም ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ ለአንድም አካል ሊሆን አይችልም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ሰው በታመመ ወይም ጉዞ በወጣ ወቅት ሀገሩ እያለና ጤናማ ሳለ እንደሚያደርገው አጅር ይጻፍለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሰውዬው አማኝ ሆኖ ያነጋና ከሀዲ ሆኖ የሚያመሽበት፤ ወይም አማኝ ሆኖ ያመሽና ከሀዲ ሆኖ የሚያነጋበት፤ እምነቱንም በአለማዊ ሸቀጥ እስከመሸጥ የሚያደርሱ የድቅድቅ ጨለማ ቁራጭ የመሰሉ ፈተናዎች ከመምጣታቸው በፊት በመልካም ስራ ተቻኮሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለትን ሰው ሃይማኖቱን ያስገነዝበዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችን ነገር ከኛ ሰምቶ እንደሰማው አድርጎ ያደረሰ ሰው አላህ ያብራው። ከሰማው ሰው የበለጠ (የሰማውን አብልጦ) የሚጠብቅ ስንትና ስንት ሰው አለ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ዕውቀትን ዑለሞችን ልትፎካከሩበት (በሊቃውንት ፊት ለመታየት)፣ ቂሎችን ልትሟገቱበት
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ሰው ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሶሀቦች ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አስር የቁርኣን አንቀፆችን ተምረው በተማሩት አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀትና ተግባር ሳይረዱ ሌላ ተጨማሪ አስር አንቀፆችን አይማሩም ነበር
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት ምንዳ ደግሞ በአስር አምሳያዋ (ትባዛለች።)
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እንደነበርከው አሳምረህ አንብብ! (ጀነት ውስጥ) ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ ወደ ቤተሰቡ የተመለሰ ጊዜ ሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎችን ቢያገኝ ያስደስተዋልን?
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ይህንን ቁርአን ተጠባበቁት! የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ እርሱ (ቁርአን) ግመል ከታሰረችበት (ፈታ) ከምታመልጠው የበለጠ በጣም የሚያመልጥ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ። ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ የሚቀራበት ቤትን ይሸሻል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" አሉኝ። "{አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} [አልበቀራህ: 255]" (አያተል ኩርሲይ) አልኩኝ። እሳቸውም ደረቴን በመምታት "በአላህ እምላለሁ! እውቀት ያስደስትህ አቡ ሙንዚር!" አሉኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾችን የሸመደደ ሰው ከደጃል ይጠበቃል።" በሌላ ዘገባ "ከሱረቱል ከህፍ መጨረሻ አስር አንቀጾች…
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'ዱዓእ እሱ አምልኮ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም ሁኔታቸው አላህን ያወሱ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ወንጀልም ሆነ ዝምድና መቁረጥ የሌለበትን ዱዓ የሚያደርግ አንድም ሙስሊም የለም በዛች ዱዓው ምክንያት አላህ ከሶስት ነገሮች አንዱን የሚሰጠው ቢሆን እንጂ: ወይ የለመነው በፍጥነት ይሰጠዋል ፤ ወይ ልመናው ለመጪው ዓለም መልካም ምንዳ ማደለቢያ ይሆንለታል፤ ወይም የለመነውን ጉዳይ የሚያክል መጥፎ ነገር ከሱ ዞር ያስደርግለታል። " ሶሀቦችም " ስለዚህ (ዱዓእ) እናብዛ?" አሉ። እሳቸውም "(ዱዓእ ካበዛችሁ) የአላህ ስጦታም እጅግ ይበዛል።" አሏቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህን በጠየቃችሁ ጊዜ ፊርደውስን ጠይቁት።
عربي እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ያ ሙቀሊበል ቁሉብ ሠቢት ቀልቢ ዐላ ዲኒክ" (አንተ ልቦናን ገለባባጭ የሆንክ ጌታ ሆይ! ልቤን በሃይማኖትህ ላይ አፅናት) ማለትን ያበዙ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አልላሁመ አስሊሕ ሊ ዲኒለዚ ሁወ ዒስመቱ አምሪ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አልላሁመ ኢኒ አስአሉከ ሚነል ኸይሪ ኩሊህ፣ ዓጂሊሂ ወአጂሊህ፣ ማ ዓሊምቱ ሚንሁ ወማለም አዕለም፣ ወአዑዙ ቢከ ሚነ ሸሪ ኩሊህ፣ ዓጂሊሂ ወአጂሊህ ማዓሊምቱ ሚንሁ ወማለም አዕለም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ያረጀ ልብስ እንደሚደክመው ሁሉ ኢማንም በአንዳችሁ ልብ ውስጥ ይደክማል። አላህ ኢማንን በልባችሁ ውስጥ እንዲያድስ ለምኑት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በአሏህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት እና በነቢዩ ሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው የኢማንን ጥፍጥና አጣጥሟል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከየሁሉም ሶላት መጠናቀቂያ ላይ 'አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ፣ ወሹክሪከ፣ ወሑስኒ ዒባደቲክ' ማለትን እንዳትተው አደራ እልሃለሁ።" አሉኝ።» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።) ማለት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ አብዝተው ያደርጉት የነበረው ዱዓ 'አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበን-ናር' የሚለውን ነበር።" (ትርጉሙም: ጌታችን አላህ ሆይ! በዱንያ መልካሙን ስጠን፤ በመጨረሻው ዓለምም መልካሙን ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።) ማለት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በላጩን ሥራችሁ፣ ንጉሳችሁ ዘንድ የጠራችውን ሥራችሁ፣ ደረጃችሁንም ከፍ የምታደርገውን ስራችሁን፣
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በርግጥም ስለ ትልቅ ጉዳይ ነው የጠየቅከኝ፤ ጉዳዩ አላህ በርሱ ላይ ላቀለለለት ሰው ቀላል ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲግፋር) አለቃ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አልላሁመ ቢከ አስበሕና ወቢከ አምሰይና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
‹ሶስት ጊዜ 'ቢስሚላሂለዚ ላየዱሩ መዐስሚሂ ሸይኡን ፊልአርዲ ወላፊስሰማእ ወሁወስ'ሰሚዑል ዐሊም' (ትርጉሙም: በዚያ ከስሙ ጋር በምድርም ይሁን በሰማይ ምንም ነገር የማይጎዳ በሆነው እንዲሁም ሰሚና አዋቂ በሆነው አላህ ስም።) ያለ ሰው እስኪነጋ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'ሱረቱል ኢኽላስ እና ሁለቱን መጠበቂያዎች (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱን-ናስን) ስታመሽና ስታነጋ ሶስት ጊዜ ካልክ ለሁሉም ነገር ይበቁሃል።' አሉኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላሁመ አዑዙ ቢሪዷከ ሚን ሰኸጢክ፣ ወቢሙዓፋቲከ ሚን ዑቁበቲክ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚንክ፣ ላኡሕሲ ሠናአን ዐለይክ አንተ ከማ አሥነይተ ዐላ ነፍሲክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ከቁጣህ በውዴታህ፣ ከቅጣትህ በይቅር ባይነትህ እጠበቃለሁ፤ ከአንተ በአንተ እጠበቃለሁ፤ አንተ እራስህን ያወደስከውን ያህል ላወድስህ አልችልም።" ማለት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ንግግሮች አራት ናቸው። 'ሱብሓነላህ' (አላህ ሆይ! ጥራት ተገባህ) 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው።) 'ላኢላሃ ኢለላህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) 'አሏሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) በማንኛቸውም ብትጀምር አይጎዳህም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አስር ጊዜ 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር' ያለ ሰው
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ "ጥራት ምስጋና ለአላህ ይገባው።" ያለ ሰው (የወንጀሉ ብዛት) የባህር ዓረፋ አምሳያ ቢሆን እንኳ ወንጀሉ ይታበስለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለው በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
''ሱብሓነሏህ ወልሐምዱሊላህ ወላኢላሃ ኢለሏህ ወሏሁ አክበር' ማለቴ ፀሀይ የወጣችበት ክልል ሁሉ (ከሚሰጠኝ) የበለጠ ወደእኔ እጅግ ተወዳጅ ነው።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሐምዱሊላህ' ማለት ነው።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በአንድ ስፍራ ላይ አርፎ ከዚያም ‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ አትታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቀ (ምሉዕ በሆኑ የአላህ ቃላት ከፈጠራቸው ጎጂ ነገሮች እጠበቃለሁ)› ያለ ሰው ከዛ ስፍራ እስኪንቀሳቀስ ድረስ አንዳችም አይጎዳውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
‹አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ: 'አልላሁምመፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲከ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) ይበል። የወጣ ጊዜም ‘አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል።›
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ሰው ወደ ቤቱ ሲገባ በሚገባበት ወቅትም በሚበላበት ወቅትም አላህን ካወሳ ሰይጣን (ለባልደረቦቹ) 'ማደሪያም እራትም የላችሁም።' ይላል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
(ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ለሁልሙልኩ ወለሁልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር) የሚለውን ውዳሴ በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ያለ ሰው
عربي እንግሊዝኛ ባንጋሊኛ
የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች ከኔ ተከታዮች መካከል አንድ ሰው ይመርጣል
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከወንጀል ትንሽም ሆነ ትልቅ የሰራሁት ቢሆን እንጂ አልተውኩትም! " አለ። እርሳቸውም "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ትመሰክር የለምን?
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
።" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችን ለመናገር እጅግ የሚከብደንን ነገር ነፍሳችን ውስጥ እናገኘዋለን (በውስጣችን ይሰማናል)" እሳቸውም፦ "ይህን (በነፍሳችሁ ውስጥ) አገኛችሁን?" አሏቸው። እነሱም፦ "አዎን" አሉ። "ይህ ግልፅ ኢማን ነው።" በማለት መለሱላቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የሰይጣንን ተንኮል ወደ ጉትጎታ የመለሰው አላህ ምስጋና ይገባው።" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የሥራ ዓይነቶች ስድስት ሲሆኑ፤ የሰው ዓይነቶች ደግሞ አራት ናቸው። (የሥራ ዓይነቶች) ሁለቱ (ጀነትና እሳትን) የሚያስከትሉ፣ አምሳያን በአምሳያው የሚያስመነዱ፣ በአስር ተባዝታ የምታስመነዳ መልካም ሥራ፣ በሰባት መቶ ተባዝታ የምታስመነዳ መልካም ሥራ ናቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የሙናፊቅ ምሳሌው በሁለት (የፍየል) መንጎች መካከል እንደዋለለች ፍየል ነው። አንድ ጊዜ ወደ አንዱ ሌላ ጊዜም ወደ ሌላኛው ትሄዳለች።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከሰዓቲቱ (ቂያማ) ምልክቶች መካከል ዕውቀት ይነሳል፣ መሀይምነት ይስፋፋል፣ ዝሙት ይበረክታል፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት ይበዛል፣ ለሀምሳ ሴቶች አንድ (ወንድ) አስተዳዳሪ እስኪሆን ድረስ ወንዶች አንሰው ሴቶች ይበዛሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አይሁዶችን ሳትዋጉና ከኋላው አንድ አይሁድ የተደበቀበት ድንጋይ ሙስሊሙ ሆይ! ይህ አይሁድ ከኋላዬ አለ ግደለው ሳይል ሰዓቲቱ አትቆምም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ፀሀይ በመግቢያዋ እስክትወጣ ድረስ ሰዓቲቱ አትቆምም። ከመግቢያዋ የወጣችና ሰዎች የተመለከቷት ጊዜ ሁሉም ያምናሉ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እኔ ሐውድ (ኩሬ) ላይ ሁኜ ከናንተ መካከል ወደ እኔ የሚመጣን እመለከታለሁ። በአቅራቢያዬ ያሉ ሰዎች (እንዳይጠጡ) ይያዛሉ። እኔም "ጌታዬ ከኔ ከኡመቴ ናቸው’እኮ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! መጠጫ እቃው ከሰማይ ከዋክብት ቁጥር የበዛ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ስንፍናና ጮሌነት ወይም ጮሌነትና ስንፍና ሳይቀር ሁሉ ነገር በአላህ ውሳኔ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ አንድ ባሪያ በአንድ ቦታ እንዲሞት የወሰነ ጊዜ ወደዚያ ስፍራ የሚሄድበትን ምክንያት ያደርግለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የመጽሐፍ ባለቤቶች (በሚተረጉሙላችሁ) አትመኑዋቸውም አታስተባብሏቸውም {በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርአን) አመንን………} በሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ የቀጥተኛውን መንገድ ምሳሌ አደረገ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ቁርኣን የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አርባ ዓመታቸው ላይ ሳሉ ወረደ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
{ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} እስክትወርድ ድረስ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የምዕራፎችን መለያ አያውቁም ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ቁርኣንን ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነብ ምፅዋትን በይፋ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው፤ ቁርኣንን በዝግታ የሚያነብ ምፅዋትን በድብቅ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የጎዳ ሰው አላህም ይጎዳዋል ፤ ያስጨነቀንም አላህም ያስጨንቀዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'አላህ ጥንቁቅ፣ (ከሰዎች) የተብቃቃና ድብቅ የሆነን ባሪያ ይወዳል።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሽቶን አይመልሱም ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የኮኮብ እውቀትን (በትንሹም) የቀሰመ ሰው ከፊልን ጥንቆላ ቀስሟል። (የኮኮብ እውቀት መቅሰሙን) በጨመረ ቁጥር (ጥንቆላውም) ይጨምራል።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በግመል አንገት ላይ (የታሰረ) የቀስት ገመድ ወይም ገመድ የተቆረጠ ቢሆን እንጂ ምንም እንዳይቀር!'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ይህቺ ጂኒ የሚሰርቃት የእውነት ንግግር ናት። በወዳጁ ጆሮ ውስጥም ዶሮ ጩኸቷን እንደምትደጋግመው ይደጋግምለታል። በዚህች እውነት ውስጥም ከመቶ ውሸት በላይ ይቀላቅሉበታል።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ የጉዳይ ጊዜ ኹጥባን (ኹጥበቱል ሓጃህ) አስተማሩን
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ