عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ نَسِيَ وَهُوَ صَائِمٌ، فَأَكَلَ أَوْ شَرِبَ، فَلْيُتِمَّ صَوْمَهُ، فَإِنَّمَا أَطْعَمَهُ اللهُ وَسَقَاهُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1155]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይሙላ። ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1155]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የግዴታ ጾም ወይም የሱና ጾም ፁሞ ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይሙላ እንዳያፈጥር ብለው ገለፁ። ምክንያቱም ማፍጠርን አስቦ ሳይሆን ይህ (በመርሳቱ ምክንያት) አላህ የሰጠው ያበላው ያጠጣው ሲሳይ ነውና።