የነቢዩ ሐዲሦች እና ትርጉሞቻቸው ኢንሳይክሎፒዲያ ፕሮጀክት:
በእስልምና ትምህርቶች ውስጥ በብዛት የሚዘወተሩ የነቢዩን ሐዲሶች በመምረጥ፤ በቀላልና በተሟላ ሁኔታ በማብራራት፤ በመቀጠልም ጥብቅ የሆኑ ሂደቶችን በመከተል በከፍተኛ ጥራት ወደተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች በመተርጎም በሁሉም የመገናኛ ዘዴዎች በነፃ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ የተቀናጀ ፕሮጀክት ነው።.
ዓላማዎች:
- ለነቢዩ ሐዲሶች ትርጉም አስተማማኝ፣ የዘመነ፣ ነፃና ዓለም አቀፋዊ የሆነ ዋቢ (ምንጭ) መፍጠር.
- ተርጓሚዎች በትርጉም ሥራ ሂደት ላይ ሳሉ የሚረዷቸውን የሐዲሥ ትርጉሞች የኤሌክትሮኒክ ማህደር (ማህደረ-ትውስታ) ማዘጋጀት.
- የትርጉም ሥራዎቹን ለታለሙ ተጠቃሚዎች በሚገኙ አማራጮች ሁሉ ተደራሽ ማድረግ.
የኢንሳይክሎፒዲያው ልዩ መገለጫዎች:
- ሁሉን አቀፍነት.
- በነፃ መሆኑ.
- የትርጉም ብዝሃነት.
- ቀጣይነት ያለው መሻሻል (መዘመኑ).
- ጥራትና ጥንቃቄ (ጥንቅቅ ያለ ሥራ) መሆኑ.
የዝግጅት እና የዕድገት እርከኖች:
- ኢንሳይክሎፒዲያውን በዐረብኛ ቋንቋ የመገንባት እርከን.
- ኢንሳይክሎፒዲያውን ወደ ሌሎች ቋንቋዎች የመተርጎም እርከን.
- ኢንሳይክሎፒዲያውን በዲጂታል መንገድ ተደራሽ የማድረግ እና የማሰራጨት እርከን.
- ኢንሳይክሎፒዲያውን እና ትርጉሞቹን በየጊዜው የማበልጸግ እና የማዘመን እርከን.