የሓዲሦች ዝርዝር

(ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አላህ እንዲህ ብሏል: ‹ሁሉም የአደም ልጅ ስራ ለርሱ ነው ፆም ሲቀር፤ ፆም ለኔ ነው። በርሱ የምመነዳውም እኔው ነኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሌላ ጊዜያት ለአምልኮ ከሚጥሩት የተለየ በመጨረሻዎቹ አስሩ የረመዷን ቀናት ይጥሩ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ፍፁም ወዳጄ የሆኑት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ነገሮች ላይ አደራ ብለውኛል። ከሁሉም ወር ሶስት ቀናት በመጾምን፣ የዱሓን ሁለት ረከዓ በመስገድንና ከመተኛቴ በፊት ዊትር መስገድን አደራ ብለውኛል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ጨረቃን ባያችሁ ጊዜ ፁሙ! ባያችሁት ጊዜ ፆም ፍቱ! ከተጋረደባችሁ ደሞ ልኩን ገምቱለት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የጋብቻን ጣጣ የቻለ ሰው ያግባ! ጋብቻ አይንን ሰባሪና ብልትን ጠባቂ ነውና። ጋብቻን ያልቻለ ሰው መፆም አለበት። ፆም ለርሱ ማኮላሺያ (የጾታዊ ፍላጎቱን የሚቆርጥለት) ነውና።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። እጅግ በጣም ቸር የሚሆኑትም ጂብሪል በሚያገኛቸው ወቅት በረመዷን ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን የጾመ ሰው አላህ ፊቱን ከእሳት ሰባ ዓመታት ያርቀዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሰዎች ማፍጠርን እስካቻኮሉ ድረስ መልካም ላይ ከመሆን አይወገዱም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጋር ሰሑር በላን። ከዚያም ወደ ሶላት ቆሙ። እኔም (አነስም ለዘይድ) "በአዛንና በሰሑር መካከል ምን ያክል ወቅት ነበር?" አልኩኝ። እርሱም (ዘይድም)፦ "ሃምሳ አንቀፅ የሚቀራበት ያህል" አለኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ህይወታቸውን እስከወሰደባት ጊዜ ድረስ የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶችን ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር። ከዚያም ከርሳቸው ህልፈት በኋላ ባለቤቶቻቸው ኢዕቲካፍ አድርገዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሰሑር ተመገቡ! በሰሑር ውስጥ በረከት አለ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ከረመዷን አንድ ቀንም ሆነ ሁለት ቀን በፊት ቀድማቹህ አትፁሙ። ነገር ግን ያስለመደው ጾም የነበረበት ሰው ከሆነ ይፁመው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይሙላ። ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ዒድን ከዑመር ቢን ኸጧብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ጋር ለመስገድ ተገኘሁ። እንዲህም አሉ: "እነዚህ ሁለት ቀናቶች የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመጾም የከለከሉት ቀናቶች ናቸው። (እነርሱም) ከጾማችሁ የምትፈቱበት ቀን (ዒድ አልፊጥር) እና ሌላኛው ቀን ደግሞ ከእርዳችሁ የምትበሉበት የሆነው ቀን (ዒደል አድሓ) ናቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ለይለቱል ቀድርን በረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶች በጎደሎ ቁጥሮቹ ውስጥ ፈልጓት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በህልማችሁ በመጨረሻዎቹ የረመዳን ሰባት ቀናት ሆና ማየታችሁ ህልማችሁ ከእውነታው ጋር ገጥማለች ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ ለይለቱል ቀድርን የሚፈልግ የሆነ ሰው በመጨረሻዎቹ የረመዳን ሰባት ቀናት ውስጥ ይፈልጋት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ሌሊቱን ህያው ሆነው ያሳልፋሉ፤ ቤተሰባቸውንም ያነቃሉ፤ ይበረቱና ሽርጣቸውንም ያጠብቁ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አመቱን ሙሉ የጾመ አልጾመም። በወር ሶስት ቀን መጾም አመቱን ሙሉ እንደመጾም ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ረመዳን የገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የእሳት በሮችም ይዘጋሉ፤ ሰይጣኖችም ይጠፈነጋሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ