عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«قَالَ اللَّهُ: كُلُّ عَمَلِ ابْنِ آدَمَ لَهُ، إِلَّا الصِّيَامَ، فَإِنَّهُ لِي وَأَنَا أَجْزِي بِهِ، وَالصِّيَامُ جُنَّةٌ، وَإِذَا كَانَ يَوْمُ صَوْمِ أَحَدِكُمْ فَلاَ يَرْفُثْ وَلاَ يَصْخَبْ، فَإِنْ سَابَّهُ أَحَدٌ أَوْ قَاتَلَهُ، فَلْيَقُلْ إِنِّي امْرُؤٌ صَائِمٌ، وَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ، لَخُلُوفُ فَمِ الصَّائِمِ أَطْيَبُ عِنْدَ اللَّهِ مِنْ رِيحِ المِسْكِ، لِلصَّائِمِ فَرْحَتَانِ يَفْرَحُهُمَا: إِذَا أَفْطَرَ فَرِحَ، وَإِذَا لَقِيَ رَبَّهُ فَرِحَ بِصَوْمِهِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1904]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አላህ እንዲህ ብሏል: ‹ሁሉም የአደም ልጅ ስራ ለርሱ ነው ፆም ሲቀር፤ ፆም ለኔ ነው። በርሱ የምመነዳውም እኔው ነኝ።› ፆም ጋሻ ነው። አንዳችሁ የፆም ቀኑ የሆነ ጊዜ ፀያፍ ቃልንም አይናገር አይጩህም። አንድ ሰው ከተሰዳደበው ወይም ከተጋደለው እኔ ፆመኛ ሰው ነኝ ይበል። የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! የፆመኛ ሰው የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ ከሚስክ ሽታ የበለጠ ታውዳለች። ፆመኛ የሚደስትባቸው ሁለት ደስታ አሉት። ሲያፈጥርም ይደሰታል። ጌታውን የተገናኘ ጊዜም በመፆሙ ይደሰታል።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1904]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በሐዲሠል ቁድስ እንዲህ እንደሚል ተናገሩ:-
ሁሉም የአደም ልጅ መልካም ስራ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ይነባበራል ፆም ሲቀር፤ ፆም ይዩልኝ የማይገባበት ስራ ነውና ለኔ ነው። እኔ ነኝ በርሱ የምመነዳው፤ የምንዳውን መጠንም ይሁን የአጅሩን መነባበር መጠን በማወቅ የተነጠልኩት እኔ ብቻ ነኝ።
ቀጥለው (ፆም ጋሻ ነው) አሉ። ከእሳት የሚጠብቅ ጋሻ፣ መሸሸጊያና መጠበቂያ ነው። ፆም ወንጀል ላይ ከመውደቅ ስሜትን የሚያቅብ ነው። እሳት በስሜቶች የተከበበች ናትና።
(አንዳችሁ የፆም ቀኑ የሆነ ጊዜ ፀያፍ ቃልን አይናገር) በግንኙነት ጉዳይም ይሁን ወደ ግንኙነት በሚያነሳሱ ነገሮች፤ በጥቅሉ የትኛውንም ፀያፍ ንግግር አይናገር።
(አይጩህም) በክርክርና በጩኸት አይናገር።
በረመዷን (አንድ ሰው ከተሰዳደበው ወይም ከተጋደለው) ከርሱ ሊቆጠብ ይከጀላልና እኔ ፆመኛ ሰው ነኝ ይበል። ሰውዬው ካልተጋደልኩ ብሎ ከደረቀ ሰው ሊያጠቃው ሲመጣ እንደሚያደርገው በቀላል መልኩ ይከላከለው።
ቀጥለው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በፆም ምክንያት የተለወጠ የፆመኛ አፍ ጠረን መዓዛው የትንሳኤ ቀን አላህ ዘንድ ‐እናንተ ዘንድ ካለው የሚስክ መአዛ የበለጠ‐ እንደሚያውድ፤ ምንዳው ደሞ በጁመዓና በዚክር መቀማመጥ ወቅት መቀባቱ ተወዳጅ ከሆነው ሚስክ የበለጠ ምንዳም እንደሚያስገኝ ነፍሳቸው በእጁ በሆነው ጌታ ምለው ተናገሩ።
ፆመኛ የሚደሰትባቸው ሁለት ደስታዎች አሉት: በሚያፈጥር ወቅት ማፍጠሩ ተፈቅዶለት አፍጥሮ ረሃቡና ጥሙ በመወገዱ፣ ፆሙ በመሙላቱና አምልኮው በመጠናቀቁ፣ በጌታው ማቅለያና ለቀጣይ ፆሙ ማገዣ በመቅመሱ ይደሰታል።
(ጌታውን የተገናኘ ጊዜም በፆሙ ይደሰታል።) በምንዳውና በክፍያው ይደሰታል።