عَن عَبْدِ اللَّهِ بنِ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: كُنَّا مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ:
«مَنِ اسْتَطَاعَ البَاءَةَ فَلْيَتَزَوَّجْ، فَإِنَّهُ أَغَضُّ لِلْبَصَرِ، وَأَحْصَنُ لِلْفَرْجِ، وَمَنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَعَلَيْهِ بِالصَّوْمِ، فَإِنَّهُ لَهُ وِجَاءٌ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1905]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ሳለን እንዲህ አሉ:
"የጋብቻን ጣጣ የቻለ ሰው ያግባ! ጋብቻ አይንን ሰባሪና ብልትን ጠባቂ ነውና። ጋብቻን ያልቻለ ሰው መፆም አለበት። ፆም ለርሱ ማኮላሺያ (የጾታዊ ፍላጎቱን የሚቆርጥለት) ነውና።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1905]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ግንኙነትንና የጋባቻን ጣጣ የቻለን ሰው እንዲያገባ አነሳሱ። ይህም ጋብቻ አይንን ከሐራም ጠባቂና ብልቱንም እጅግ በጣም ጠብቆለት ዝሙት ላይ ከመውደቅ ስለሚከለክለው ነው። የጋብቻን ጣጣ ሳይችል ግንኙነትን የቻለ ሰውም መጾም ይገባዋል። ፆም የብልትን ስሜት እና መጥፎ የዘር ፈሳሽን ይቆርጣልና።