عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤْمِنينَ رَضِي اللهُ عنْها قَالَتْ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«أَيُّمَا امْرَأَةٍ نَكَحَتْ بِغَيْرِ إِذْنِ مَوَالِيهَا، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ -ثَلَاثَ مَرَّاتٍ- فَإِنْ دَخَلَ بِهَا فَالْمَهْرُ لَهَا بِمَا أَصَابَ مِنْهَا، فَإِنْ تَشَاجَرُوا فَالسُّلْطَانُ وَلِيُّ مَنْ لَا وَلِيَّ لَهُ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 2083]
المزيــد ...
የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ከወሊዩዋ (አሳዳጊዋ) ፈቃድ ውጪ ያገባች ማንኛዋም ሴት ጋባቻዋ ውድቅ ነው። (ንግግራቸውን ሶስት ጊዜ ደጋግሙት) እርሷን ከተገናኘም በመንካቱ ምክንያት መህሯ የራሷ ነው። ወሊዮች ከተጨቃጨቁም ወሊይ ለሌለው ሰው የሙስሊሞች መሪ ወሊዩ ነው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 2083]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሴት ልጅ ያለ ወሊዮቿ ፍቃድ ራሷን ማጋባቷን ከለከሉ። ጋብቻዋም ውድቅ ነው የሚሆነው። ጋብቻዋ እንዳልተፈፀመ ለመግለፅም ሶስት ጊዜ ደጋገሙት።
ያለ ወሊዩዋ ፈቃድ አግብቷት የተገናኛትም በመገናኘቱ ምክንያት ለርሷ ሙሉ መህር ይሰጣታል።
በመቀጠል የወሊዮች ደረጃ እኩል ሆኖ ጋብቻን በማሰሩ ዙሪያ ወሊዮች ከተጨቃጨቁ ጋብቻውን የሚያስረው የቀደመው ነው። ይህም ጥሩ ነገር አይቶላት ከሆነ ነው። ወሊዩዋ ከማጋባት ከታቀበ ወሊይ እንደሌላት ትቆጠራለች። መሪው ወይም ዳኛው ወይም የመሳሰሉት ወሊዩዋ ይሆናሉ። ያለበለዚያ ወሊይ እያለ መሪ ወሊይነት የለውም።