عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي لله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَا يَفْرَكْ مُؤْمِنٌ مُؤْمِنَةً، إِنْ كَرِهَ مِنْهَا خُلُقًا رَضِيَ مِنْهَا آخَرَ» أَوْ قَالَ: «غَيْرَهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1469]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አንድ አማኝ ወንድ አንዲትን አማኝ እንስት አይጥላ። ከርሷ አንድ ባህሪዋን ቢጠላ እንኳ ሌላ የሚወደው ባህሪ አላትና።" ወይም "ከርሱ ውጪ ያለን ባህሪ… " ብለዋል።
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1469]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባል ሚስቱን ወደ መበደል፣ ወደ መተውና ችላ ወደማለት የሚያደርስ የሆነ ጥላቻን ከመጥላት ከለከሉ። የሰው ልጅ በጉድለት ላይ የተፈጠረ ነው። በሚስቱ ላይ መጥፎ ባህሪዋን ቢጠላ እንኳ ሌላ መልካም ባህሪን እርሷ ላይ ያገኛል። ከርሱ ጋር የሚስማማውን መልካም ባህሪ ይውደድላትና የማይወድላትን መጥፎ ባህሪ ደግሞ ይታገስ። ይህም እንዲታገስ የሚያደርገውና ወደመለያየት የሚያደርስ ጥላቻን ከመጥላት የሚታደግ ነው።