عن عبد الله بن عمرو رضي الله عنهما أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«الدُّنْيَا مَتَاعٌ، وَخَيْرُ مَتَاعِ الدُّنْيَا الْمَرْأَةُ الصَّالِحَةُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1467]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"ዱንያ መጣቀሚያ ናት። ከዱንያ መጣቀሚያዎች ምርጡ መልካም ሚስት ናት።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1467]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱንያም ውስጧ ያሉ ነገሮችም በሙሉ ጊዜያዊ መጠቀሚያዎች ሆነው ከዚያም የሚጠፉ መሆናቸውን፤ በላጩ መጣቀሚያም ሲያያት የምታስደስተው፣ ሲያዛት የምትታዘዘው፣ ሲርቅ ነፍሷንና ንብረቱን የምትጠብቅ መልካም ሚስት መሆኗን ተናገሩ።