+ -

عَنْ عُقْبَةَ بْنِ عَامِرٍ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِيَّاكُمْ وَالدُّخُولَ عَلَى النِّسَاءِ» فَقَالَ رَجُلٌ مِنَ الأَنْصَارِ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَفَرَأَيْتَ الحَمْوَ؟ قَالَ: «الحَمْوُ المَوْتُ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5232]
المزيــد ...

ከዑቅበህ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ሴቶች ጋር ከመግባት ተጠንቀቁ!" አንድ ከአንሷር የሆነ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለባል ቅርብ ዘመዶች ንገሩኝ እስኪ?" አለ። እርሳቸውም "የባል ቅርብ ዘመድማ ሞት ነው።" አሉ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5232]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከእንግዳ ሴቶች ጋር ከመቀላቀል እንዲህ በማለት አስጠነቀቁ "በሴቶች ላይ ከመግባትና ሴቶችም እናንተ ዘንድ እንዳይገቡ ነፍሳችሁን ጠብቁ!"
አንድ የአንሷር ሰውዬም እንዲህ አለ: እስኪ ንገሩኝ የባል ወንድም፣ የወንድሙ ልጅ፣ አጎቱ፣ የአጎቱ ልጅ፣ የእህቱ ልጅና የመሳሰሉት ባታገባ ኖሮ ልታገባቸው የሚፈቀዱላት የባል ቅርብ ዘመዶች ቢገቡስ ይፈቀዳልን?
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ሞትን እንደምትጠነቀቁት እርሱንም ተጠንቀቁት! ከባል ዘመዶች ጋር ገለል ብሎ ማሳለፍ ለሃይማኖት ፈተናና ጥፋት የሚመራ ነው። ከአባቱና ከልጆቹ ውጪ ያሉ የባል ቅርብ ዘመዶችን መከልከል ከሌላው ባዳ ወንድ የበለጠ የተገባ ነው። ይህም ከሌላ ባዳ ጋር ለብቻ ከምታሳልፍበት ጊዜ ይልቅ ከባል ቅርብ ዘመድ ጋር ለብቻ የማሳለፍ እድሉ የበዛ ስለሆነ ከሌላው በበለጠ ከርሱ ጋር መጥፎ ነገር መከሰቱ ስለሚገመትና ያለምንም አውጋዥ ወደ ሴቷ መድረስና ከርሷ ጋር ለብቻ ማሳለፍ ስለሚችል ፈተና የመከሰት እድሉም የሚመች ነው። በተለምዶ የባል ወንድም የወንድሙ ሚስት ብቻዋን እያለች መግባት ቸል የሚባል ጉዳይ ስለሆነ ፈተና መከሰቱ የማይቀር ጉዳይ ነው። ከባዳ ወንድ ጋር ለብቻ ማሳለፍማ የሚጠነቀቁት ጉዳይ ነው። ከርሱ በተቃራኒ ከባል ዘመድ ጋር ለብቻ የማሳለፍ አፀያፊነትና የሚያስከትለው ችግር ግን ከሞት ጋር ይመሳሰላል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ዝሙት ላይ የመውደቂያን መዳረሻ ለመዝጋት ወደ ባዳ ሴቶች ከመግባትና ከነርሱ ጋር ለብቻ ከማሳለፍ መከልከሉን እንረዳለን።
  2. ይህ ክልከላ የሴቷ ቅርብ ዘመዶች ያልሆኑን የባል ወንድምንና ቅርብ ዘመዶቹን ጨምሮ ባዳ ወንዶችን ባጠቃላይ የሚጠቀልል ነው። (ባል በሌለበት) መግባቱ ብቻ ከርሷ ጋር መገለልን ማስፈረዱ የማይቀር ጉዳይ ነው።
  3. መጥፎ ነገር ላይ መውደቅን በመፍራት ብዙሃን ስህተት ላይ የሚወድቁበትን ስፍራ መራቅ ይገባል።
  4. ነወዊ እንዲህ ብለዋል: «የቋንቋ ምሁራን ባጠቃላይ እንደተስማሙት "አሕማእ" ማለት የባል ቅርብ ዘመዶች ናቸው። አባቱ፣ አጎቱ፣ ወንድሙ፣ የወንድሙ ልጅ፣ የአጎቱ ልጅና የመሳሰሉት ማለት ነው። "አኽታን" ማለት ደግሞ የሚስት ቅርብ ዘመዶች ናቸው። "አስሃር" የሚለው ቃል ደግሞ ለሁለቱም የሚውል ስም ነው።»
  5. የባል ዘመድ ከሞት ጋር አመሳስለው የመግለፃቸው ምስጢር:- ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ዐረቦች የሚጠሉትን ነገር በሞት ይመስሉታል። የመመሳሰሉም መልክ ከባል ዘመድ ጋር ወንጀል ከተፈፀመ በዲን በኩል እንደሞት ነው፤ ወንጀል ከተፈፀመም ከባል ዘመድ ጋር ተገልላ ያሳለፈችው የመወገር ግዴታ ስላለባት ትሞታለች፤ ባል ቅናቱ ለፍቺ ከገፋፋውም ከባሏ መለየቷ ለሴቷ ጥፋት ነው።»