عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ الدُّنْيَا حُلْوَةٌ خَضِرَةٌ، وَإِنَّ اللهَ مُسْتَخْلِفُكُمْ فِيهَا، فَيَنْظُرُ كَيْفَ تَعْمَلُونَ، فَاتَّقُوا الدُّنْيَا وَاتَّقُوا النِّسَاءَ، فَإِنَّ أَوَّلَ فِتْنَةِ بَنِي إِسْرَائِيلَ كَانَتْ فِي النِّسَاءِ».

[صحيح] - [رواه مسلم]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ (ለምለም) ናት። አላህም እንዴት እንደምትሰሩ ሊያያችሁ በውስጧ ምትኮች አድርጓችኋል። ዱንያንም ተጠንቀቁ! ሴቶችንም ተጠንቀቁ! የበኒ ኢስራኢሎች የመጀመሪያ ፈተና የተከሰተው በሴቶች ነበርና።"

Sahih/Authentic. - [Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዱንያ ስትቀመስ ጣፋጭ ስትታይ ደግሞ አረንጓዴ ለምለም ስለሆነች ሰው በርሷ እንደሚሸወድ፣ በርሷ እንደሚሰምጥና ትልቁ ጉዳዩ እንደሚያደርጋትም ገለፁ። ከፍ ያለውና ጥራት የተገባው አላህ በዚህች የዱንያ ህይወት እንዴት እንደምንሰራና ለርሱ ታዛዥ እንሆናለን? ወይስ እናምፀዋለን? የሚለውን ለመመልከት ከፊላችን ከፊሉን እንዲተካ አድርጓል። ከዚያም: "የዱንያ መጣቀሚያና ጌጧ እንዳይሸውዳችሁ፤ አላህ ያዘዛችሁን ለመተውና በከለከላችሁ ላይ ለመውደቅ እንዳያነሳሳችሁ ተጠንቀቁ! አሉ። እጅግ ትልቁ ከዱንያ ፈተናዎች መካከል መጠንቀቅ ግድ የሚሆንብንም የሴቶች ፈተና ነው። ሴት በኒ ኢስራኢሎች የወደቁበት የመጀመሪያዋ ፈተና ናት።"

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ጥንቁቅነትን አጥብቆ በመያዝ ላይና በዱንያ ውጫዊ ገፅታና ጌጧ አለመሸወድ ላይ መነሳሳቱ።
  2. ሴቶችን በማየት ወይም ከባዕድ ወንዶች ጋር መቀላቀላቸውን በማቃለል ወይም ከዚህ ውጪም ባሉ መፈተኛዎች በሴቶች ፈተና ከመውደቅ መጠንቀቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
  3. የሴቶች ፈተና ከዱንያ እጅግ ትላልቅ ፈተናዎች መካከል አንዱ ነው።
  4. ባለፉት ህዝቦች መገሰፅና ትምህርትን መውሰድ እንደሚገባ እንረዳለን። በኒ ኢስራኢሎች ላይ የተከሰተው ሌላውም ላይ ሊከሰት ይችላልና።
  5. የሴቶች ፈተና ሲባል ሚስት ከሆነች ሰውየውን ከአቅሙ በላይ በሆነ ወጪ ታስገድደውና በዚህም ዲናዊ ጉዳዮችን ከመፈለግ ጠምዳው ሙሉ ጊዜውን ዱንያን በመፈለግ ላይ እያዋለ እንዲጠፋ ታደርገዋለች፤ ባዕድ ሴት ከሆነች ደግሞ የርሷ ፈተና ከቤቷ በምትወጣ ወቅትና ከወንዶች ጋር በምትቀላቀል ጊዜ ወንዶችን ማታለሏና ከእውነት ዞር እንዲሉ ማድረጓ ነው። በተለይ ደግሞ የተራቆቱና የተገላለጡ ከሆኑ እንደየደረጃው ዝሙት ላይ ወደ ለመውደቅ ይዳርጓቸዋል። ስለዚህም የትኛውም አማኝ በአላህ ለመጠበቅና ከነርሱ ፈተና ለመዳን ከአላህ ጋር ትስስሩን ማጠንከር ይገባዋል።