عن عائشة رضي الله عنها قالت: قال النبي صلى الله عليه وسلم:
«لَا تَسُبُّوا الْأَمْوَاتَ، فَإِنَّهُمْ قَدْ أَفْضَوْا إِلَى مَا قَدَّمُوا».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 1393]
المزيــد ...
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
"ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1393]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሟቾችን መሳደብና ክብራቸውን መንካት ክልክል መሆኑን አብራሩ። ከእኩይ ስነ ምግባሮችም የሚመደብ እንደሆነ ገለፁ። ምክንያቱም ይህ ስድብ በህይወት ያሉ ሰዎችን ከመጉዳት የዘለለ ለነርሱ የማይደርሳቸው ከመሆኑም በተጨማሪ እነሱ ወዳስቀደሙት መልካምም ይሁን መጥፎ ስራቸው ደርሰዋልና።