عَنْ عَبْدِ اللهِ بنِ مَسْعُودٍ رضي الله عنه قال:
سَأَلْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: أَيُّ الذَّنْبِ أَعْظَمُ عِنْدَ اللهِ؟ قَالَ: «أَنْ تَجْعَلَ لِلهِ نِدًّا وَهُوَ خَلَقَكَ» قُلْتُ: إِنَّ ذَلِكَ لَعَظِيمٌ، قُلْتُ: ثُمَّ أَيُّ؟ قَالَ: «وَأَنْ تَقْتُلَ وَلَدَكَ؛ تَخَافُ أَنْ يَطْعَمَ مَعَكَ» قُلْتُ: ثُمَّ أَيُّ؟ قَالَ: «أَنْ تُزَانِيَ حَلِيلَةَ جَارِكَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4477]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
"ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'አላህ ዘንድ እጅግ ትልቁ ወንጀል ምንድነው?' ብዬ ጠየቅኩ። እርሳቸውም 'አላህ ፈጥሮህ ሳለ ለርሱ ቢጤን ማድረግክ ነው።' አሉ። እኔም 'ይህማ ትልቅ ነው።' አልኩኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'ልጅህን ከአንተ ጋር መብላቱን ፈርተህ መግደልክ ነው።' አሉኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'በጎረቤትህ ሚስት ላይ ዝሙት መስራትህ ነው።' አሉኝ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4477]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ እጅግ ትልቁ ወንጀል ተጠየቁ: እጅግ ትልቁ ወንጀል ትልቁ ሺርክ ነው። እርሱም ለአላህ በተመላኪነቱ ወይም በጌትነቱ ወይም በስሞቹና ባህሪያቶቹ ምሳሌ ወይም ቢጤን ማድረግክ ነው። ይህን ወንጀል አላህ ያለ ተውበት አይምረውም። ባለቤቱ በዚህ ወንጀል ላይ ሳለ ከሞተም በእሳት ውስጥ ዘውታሪ ነው። ቀጥሎም ሰውዬው ልጁን ከርሱ ጋር መብላቱን ፈርቶ መግደሉ ነው። በመሰረቱ ነፍስን መግደል ክልክል ነው። ነገር ግን ተገዳዩ የገዳዩ ዘመድ ከሆነ ወንጀሉ የከፋ ይሆናል። አሁንም በድጋሚ ገዳዩ የመግደሉ አላማ ተገዳዩ በአላህ ሲሳይ ላይ እንዳይጋራው አስቦ ከሆነ ወንጀሉ እጅግ የከፋ ይሆናል። ቀጥሎ አንድ ሰው በጎረቤቱ ሚስት ላይ ዝሙት መስራቱ ነው። እርሷ ላይ ዝሙት እስኪሰራና ታዛዡ እስክትሆን ድረስ የጎረቤቱን ሚስት ለማታለል መሞከሩ ነው። በመሰረቱ ዚና ክልክል ነው። ነገር ግን ዝሙት የተሰራባት ሸሪዓ ለነርሱ መልካም እንድንውልላቸው፣ በጎ እንድናደርግላቸውና ጥሩ ወዳጅኝት እንዲኖረን ያዘዘን በሆነው የጎረቤት ሚስት ከሆነች ወንጀሉ የከፋ ይሆናል።