+ -

عن عمر بن الخطاب رضي الله عنه قال:
بَيْنَمَا نَحْنُ عِنْدَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ذَاتَ يَوْمٍ إِذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ، شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ، لَا يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ، وَلَا يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ، حَتَّى جَلَسَ إِلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَأَسْنَدَ رُكْبَتَيْهِ إِلَى رُكْبَتَيْهِ، وَوَضَعَ كَفَّيْهِ عَلَى فَخِذَيْهِ، وَقَالَ: يَا مُحَمَّدُ، أَخْبِرْنِي عَنِ الْإِسْلَامِ، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «الْإِسْلَامُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إِنِ اسْتَطَعْتَ إِلَيْهِ سَبِيلًا» قَالَ: صَدَقْتَ، قَالَ: فَعَجِبْنَا لَهُ، يَسْأَلُهُ وَيُصَدِّقُهُ، قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنِ الْإِيمَانِ، قَالَ: «أَنْ تُؤْمِنَ بِاللهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَالْيَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ» قَالَ: صَدَقْتَ، قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنِ الْإِحْسَانِ، قَالَ: «أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ» قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنِ السَّاعَةِ، قَالَ: «مَا الْمَسْؤُولُ عَنْهَا بِأَعْلَمَ مِنَ السَّائِلِ» قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ أَمَارَتِهَا، قَالَ: «أَنْ تَلِدَ الْأَمَةُ رَبَّتَهَا، وَأَنْ تَرَى الْحُفَاةَ الْعُرَاةَ الْعَالَةَ رِعَاءَ الشَّاءِ يَتَطَاوَلُونَ فِي الْبُنْيَانِ» قَالَ: ثُمَّ انْطَلَقَ، فَلَبِثْتُ مَلِيًّا ثُمَّ قَالَ لِي: «يَا عُمَرُ، أَتَدْرِي مَنِ السَّائِلُ؟» قُلْتُ: اللهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ، قَالَ: «فَإِنَّهُ جِبْرِيلُ، أَتَاكُمْ يُعَلِّمُكُمْ دِينَكُمْ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 8]
المزيــد ...

ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
ከዕለታት አንድ ቀን የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ሳለን ድንገት ልብሱ እጅግ በጣም ነጭ የሆነ፤ ፀጉሩ ደግሞ እጅግ በጣም ጥቁር የሆነ ሰውዬ ብቅ አለ። በሱ ላይ የጉዞ ምልክት አይታይበትም፤ ከኛ ውስጥም አንድም የሚያውቀው ሰው የለም፤ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ መጥቶ ተቀመጠ። ጉልበቱን ወደ ጉልበታቸው አስጠጋ፤ መዳፎቹንም በታፋዎቹ ላይ አደረገና "ሙሐመድ ሆይ! ስለ ኢስላም ንገረኝ!" አላቸው። የአላህ መልዕክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ኢስላም ማለት ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ልትመሰክር፣ ሰላት ደንብና ስርዓቱን ጠብቀህ ልትሰግድ፣ ዘካን ልትሰጥ ፣ ረመዷንን ልትፆምና ወደርሱ መንገድን ከቻልክም የአላህን ቤት ልትጎበኝ ሐጅ ልታደርግ ነው።" አሉት። እሱም "እውነት አልክ!" አላቸው። "በሱ ተገረምን ይጠይቃቸዋልም (ጥያቄውን በትክክል እንደመለሱ) ያረጋግጥላቸዋልም።" ከዚያም፦ "ስለኢማን ንገሩኝ!" አላቸው። እሳቸውም "በአላህ፣ በመላእክቱ፣ በመጻሕፍቱ፣ በመልክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀንና በጥሩውም ሆነ መጥፎ ውሳኔዎቹም ልታምን ነው።" አሉት። እሱም "እውነት አልክ!" አላቸው። "ስለኢሕሳን (በጎ መስራት) ንገሩኝ!" አላቸው። እሳቸውም "አላህን ልክ እንደምታየው ሆነህ ልትገዛው ነው። አንተ ባታየው እንኳ እርሱ ያይሀልና።" አሉት። "ስለ ሰዓቱቱ (ቂያማ) ንገረኝ!" አላቸው። እሳቸውም "ስለርሷ ተጠያቂው ከጠያቂው የበለጠ አዋቂ አይደለም።" አሉት። "ስለ ምልክቶቿ ይንገሩኝ!" አለ። እሳቸውም "ባሪያ ጌታዋን ልትወልድ ነው ፤ ያልተጫማ፣ የታረዘ፣ ድሃና የፍየል እረኛ የሆኑ ሰዎች ለህንፃዎች ሲሽቀዳደሙ ማየትህ ነው።" አሉት። ዑመር እንዲህ አለ "ከዚያም ሄደ። የተወሰነ ጊዜ ቆየሁ። ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ዑመር ሆይ! ጠያቂው ማን እንደነበር አውቀሀልን?" አሉኝ። እኔም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አልኳቸው። እሳቸውም "እርሱ ጂብሪል ነው እምነታችሁን ሊያሳውቃችሁ መጥቷችሁ ነው።" አሉ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 8]

ትንታኔ

ዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከዕለታት አንድ ቀን ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም በሶሐቦች መካከል አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በማይታወቅ ሰው ተመስሎ እንደወጣ ይናገራሉ። ከዚህም ሰውዬ ባህሪ ልብሱ እጅግ የነጣ፣ ፀጉሩም እጅግ የጠቆረ ነበር። በሱ ላይም ድካም፣ አቧራ፣ የፀጉር መንጨባረርና የልብስ መቆሸሽ የመሰሉ የጉዞ ምልክት አይታይበትም። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ተቀምጠው ከነበሩ ታዳሚዎች መካከልም አንድም ሰው አላወቀውም። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፊት እንደተማሪ አቀማመጥ ተቀመጠ። ስለ ኢስላምም ጠየቃቸው። እሳቸውም በሁለቱ የምስክር ቃላት ማረጋገጥን፣ አምስቱ ሶላቶች ላይ መጠባበቅን፣ ለሚገባው ሰው ዘካ መስጠትን፣ የረመዷን ወር መፆምን፣ በቻለ ላይ ግዴታ የሆነውን ሐጅ መፈፀምን ያካተተውን እነዚህን ማዕዘናት በመጥቀስ መለሱለት።
ጠያቂውም "እውነት አልክ!" አለ። ሶሐቦችም ከላይ ሲታይ አጠያየቁ አለማወቁን የሚጠቁም፤ ከዛ ደግሞ ትክክለኛ መልስ እንደተመለሰለት ማረጋገጡን በማስተዋላቸው ግራ ተጋቡ።
ከዚያም ስለ ኢማን ጠየቃቸው። እሳቸውም እነዚህን ስድስት ማዕዘናት ማመንን የሰበሰበ መልስ መለሱለት። እነሱም:-አላህ በመኖሩ፣ በባህሪያቶቹ፣ መፍጠርን በመሰሉ ድርጊቶቹና በአምልኮም ብቸኛ መሆኑን ማመን፤ አላህ ከብርሃን የፈጠራቸው መላእክቶች የተከበሩ ባሮቹ መሆናቸውን፣ አላህን የማያምፁና በትእዛዙ የሚተገብሩ መሆናቸውን ማመን፤ እንደ ቁርኣን፣ ተውራት፣ ኢንጂልና ሌሎችም ከአላህ ዘንድ በመልክተኞች ላይ በወረዱ መጽሐፍት ማመን፤ የአላህን ሃይማኖት የሚያደርሱ በሆኑ መልክተኞች ማመን ከነሱም መካከል ኑሕ፣ ኢብራሂም፣ ሙሳ፣ ዒሳና የመጨረሻቸው የሆኑት ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂም ወሰለምና ሌሎችም ነቢያቶችና መልክተኞች ይጠቀሳሉ። በመጨረሻው ቀን ማመን፤ እዚህ ምውስጥም ከሞት በኋላ ያሉ በቀብርና በበርዘኽ ህይወት እንዲሁም የሰው ልጅ ከሞት በኋላ የሚቀሰቀስና የሚተሳሰብ መመለሻውም ወይ ወደ ጀነት ወይ ወደ እሳት መሆኑን ማመንንም ያካትታል። አላህ በቀደመ ዕውቀቱ መሰረት፣ ጥበቡ ባስፈረደው መልኩ በፍላጎቱ መሰረት ነገሮችን እንደወሰነና በጽሑፍም እንዳሰፈረ ማመን፤ ምድር ላይ የሚከሰቱትም በወሰናትና በፈጠራት ልክ መሆኑንም ማመን ነው። ከዚያም ስለ ኢሕሳን (ስራን ማሳመር) ጠየቃቸው። ኢሕሳን ማለት ልክ አላህን እያዩ እንደሆነ እያሰቡ አላህን መገዛት ነው። እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ባይረጋገጥለት (ባይችል) እንኳ ልክ አላህ እርሱን እያየው እንደሆነ በማሰብ አላህን መገዛት ነው። የመጀመሪያው: የ "ሙሻሀዳህ" (አሏህን እያየህ እንደሆነ እያሰብክ የምታመልክበት) ደረጃ ነው እሱም የላቀ ደረጃ ነው። ሁለተኛው ደግሞ የ "ሙራቀባህ" (አሏህ እያየኝ ነው በሚል ሃሳብ የምታመልክበት) ደረጃ ነው።
ከዚያም ሰዓቲቱ መቼ እንደሆነች ጠየቃቸው። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰዓቲቱ መከሰቻ ጊዜ አላህ በእውቀቱ ብቸኛ ከሆነበት ጉዳይ አንዱ በመሆኑ ተጠያቂውም ይሁን ጠያቂው ከፍጥረቱ መካከልም አንድም እንደማያውቀው ገለፁ።
ከዚያም ስለ ሰዓቲቱ ምልክቶች ጠየቃቸው። ከምልክቶቿ መካከል የጭን ገረዶችና ልጆቻቸው እንደሚበዙ ወይም የልጆች የእናቶቻቸውን ሐቅ አለመወጣታቸው እንደሚበዛ ይህም ከእናቶቻቸው ጋር ያላቸው መስተጋብር ልክ ከባሪያ ጋር እንዳላቸው አይነት መስተጋብር እንደሚሆን፤ ለበግ እረኞችና ለድሆች በመጨረሻው ዘመን ዱንያ ተዘርግታላቸው በህንፃ ውበትና አሰራር እንደሚፎካከሩ ገለፁ።
ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠያቂው ጂብሪል እንደነበረና የመጣውም ይህንኑ ቀጥተኛ እምነት ለሶሐቦች ሊያስተምር እንደሆነ ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht Azerisht الأوزبكية الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነ ምግባር ማማር፤ ከባልደረቦቻቸው ጋር የሚቀመጡ መሆናቸውን እነሱም ከሳቸው ጋር እንደሚቀመጡ ፤
  2. ለጠያቂ ገር መሆንና ማቅረብ የተደነገገ መሆኑን፤ ይህም ሳይጨናነቅና ሳይፈራ ለመጠየቅ እንዲመቻች ነው።
  3. ልክ ጂብሪል እውቀት ሊቀስም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፊት ስርአት ያለውን አቀማመጥ በመቀመጥ እንደተገበረ ከአስተማሪ ጋር አደብ መያዝ እንደሚገባ ፤
  4. የኢስላም ማዕዘናት አምስት የኢማን መሰረቶች ደግሞ ስድስት መሆናቸውን፤
  5. "ኢስላም" የሚለው ቃልና "ኢማን" የሚለው ቃል አንድ ላይ ሲመጡ "ኢስላም" ውጫዊ በሆኑ ነገሮች ሲተረጎም "ኢማን" ደግሞ ውስጣዊ በሆኑ ነገሮች ይተረጎማል።
  6. የኢስላም ሃይማኖት የሚበላለጡ ደረጃዎች እንዳሉት መገለፁ፤ የመጀመሪያው ደረጃ: ኢስላም ፣ ሁለተኛው: ኢማን ፣ ሶስተኛው: ኢሕሳን ነው። እርሱ (ኢሕሳን) ከፍተኛው ደረጃ ነው።
  7. የጠያቂ መሰረቱ አለማወቅ ነው። አለማወቅ ነው ለጥያቄ የሚያነሳሳው። ለዚህም ነው ሶሐቦች እየጠየቀም የመልሱን እውነተኝነት ሲያረጋግጥ የተደነቁት።
  8. እጅግ አንገብጋቢ ከሆነ ነጥብ መጀመር እንደሚገባ፤ እሳቸው ኢስላምን ሲያብራሩ በሁለቱ የምስክርነት ቃላት ነውና የጀመሩት፣ ኢማንን ሲያብራሩም በአላህ ከማመን ነውና የጀመሩት፤
  9. ጠያቂው የሚያውቀውን ነገር ሌሎችን ለማሳወቅ ሲል የእውቀት ባለቤቶችን መጠየቅ እንደሚችል፤
  10. የሰዓቲቱ እለት እውቀት አላህ በእውቀቱ ከተነጠለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው።