عَنْ أَبِي الحَوْرَاءِ السَّعْدِيِّ قَالَ: قُلْتُ لِلْحَسَنِ بْنِ عَلِيٍّ رضي الله عنهما: مَا حَفِظْتَ مِنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ؟ قَالَ: حَفِظْتُ مِنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«دَعْ مَا يَرِيبُكَ إِلَى مَا لاَ يَرِيبُكَ، فَإِنَّ الصِّدْقَ طُمَأْنِينَةٌ، وَإِنَّ الكَذِبَ رِيبَةٌ».
[صحيح] - [رواه الترمذي والنسائي وأحمد] - [سنن الترمذي: 2518]
المزيــد ...
ከአቡል ሐውራእ አስሰዕዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: ለሐሰን ቢን ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - «ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምን ሸምድደሃል? አልኩት። እርሱም: "ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን ሸምድጃለሁ አለኝ።
‹የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት እርጋታን የተላበሰ ነው። ውሸት ደሞ ጥርጣሬን የተላበሰ ነው።›"»
[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን ቲርሚዚ - 2518]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ክልክል ነው ወይስ አይደለም፣ ሐላል ነው ወይስ ሐራም ነው እያልክ የምትጠራጠርበት ንግግርና ተግባር በመተው መልካምነቱንና ፍቁድነቱን እርግጠኛ ወደሆንክበትና ወዳልተጠራጠርክበት መሄድን አዘዙ። ቀልብ እርግጠኛ በሆነበት ነገር ላይ ይረጋል። አጠራጣሪ በሆነ ነገር ደግሞ ይወዛገባል።