+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«صَلَاةُ الرَّجُلِ فِي جَمَاعَةٍ تَزِيدُ عَلَى صَلَاتِهِ فِي بَيْتِهِ وَصَلَاتِهِ فِي سُوقِهِ بِضْعًا وَعِشْرِينَ دَرَجَةً، وَذَلِكَ أَنَّ أَحَدَهُمْ إِذَا تَوَضَّأَ فَأَحْسَنَ الْوُضُوءَ، ثُمَّ أَتَى الْمَسْجِدَ لَا يَنْهَزُهُ إِلَّا الصَّلَاةُ، لَا يُرِيدُ إِلَّا الصَّلَاةَ، فَلَمْ يَخْطُ خَطْوَةً إِلَّا رُفِعَ لَهُ بِهَا دَرَجَةٌ، وَحُطَّ عَنْهُ بِهَا خَطِيئَةٌ، حَتَّى يَدْخُلَ الْمَسْجِدَ، فَإِذَا دَخَلَ الْمَسْجِدَ كَانَ فِي الصَّلَاةِ مَا كَانَتِ الصَّلَاةُ هِيَ تَحْبِسُهُ، وَالْمَلَائِكَةُ يُصَلُّونَ عَلَى أَحَدِكُمْ مَا دَامَ فِي مَجْلِسِهِ الَّذِي صَلَّى فِيهِ، يَقُولُونَ: اللهُمَّ ارْحَمْهُ، اللهُمَّ اغْفِرْ لَهُ، اللهُمَّ تُبْ عَلَيْهِ، مَا لَمْ يُؤْذِ فِيهِ، مَا لَمْ يُحْدِثْ فِيهِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 649]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
'ሰውዬው በህብረት የሚሰግደው ሶላት በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው ሶላት ሀያ ምናምን ደረጃ ትበልጣለች። ይህም አንዳቸው ዉዱእ ሲያደርግ ዉዱእን አሳምሮ ከዚያም ከሶላት በስተቀር ሳያንቀሳቅሰው ከሶላትም በስተቀር ሌላን ሳይፈልግ ወደ መስጅድ ከመጣ መስጂድ እስኪገባ ድረስ በሚራመደው እያንዳንዱ እርምጃ ልክ ለርሱ ደረጃው ከፍ ይደረግለታል፤ ወንጀሉም ከርሱ ላይ በሷው ይራገፍለታል። መስጂድ የገባ ገዜም በሶላቷ ምክንያት እስከተጠመደ ድረስ ሶላት ውስጥ ነው። አንዳችሁ በሰገደበት ስፍራ ላይ እስከዘወተረ ድረስም ሰዎችን እስካላወከና ዉዱእ እስካላጠፋ ድረስ መላእክቶች በርሱ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ። 'አላህ ሆይ እዘንለት፣ አላህ ሆይ ማረው፣ አላህ ሆይ ፀፀቱን ተቀበለው' ይላሉም።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 649]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ሙስሊም በህብረት የሰገደ ጊዜ ይህቺ ሶላቱ ቤቱ ውስጥ ወይም ሱቁ ውስጥ ከሚሰግደው ሰላት ሀያ ምናምን እጥፍ የምትበልጥ መሆኗን ተናገሩ። ቀጥለውም የዚህን ምክንያት ተናገሩ። እርሱም ሰዉዬው ዉዱእን አሟልቶና አሳምሮ አድርጎ ከዚያም ሶላትን ብቻ ፈልጎ ወደ መስጊድ እስከወጣ ድረስ በእያንዳንዷ እርምጃው ምክንያት ደረጃው ከፍ ይላል፤ ወንጀሉም ይታበስለታል። መስጂድ ገብቶም ሶላትን እየጠበቀ ከተቀመጠ ሶላትን እስከተጠባበቀበት ጊዜ ድረስ የሶላትን ምንዳና አጅር ያገኛል። መላእክቶችም የሰገደበት ስፍራ ላይ እስከተቀመጠ ድረስ ለርሱ እንዲህ እያሉ ዱዓ ያደርጉለታል፦ "አላህ ሆይ ማረው፣ አላህ ሆይ እዘንለት፣ አላህ ሆይ ፀፀቱን ተቀበለው" ይህ ግን ዉዱኡን እስካላበላሸ ወይም ሰዎችን ወይም መላእክትን የሚያውክ ነገር እስካልፈፀመ ድረስ ነው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ቤት ውስጥ ወይም ሱቅ ውስጥ ለብቻ የሚሰገድ ሶላት ትክክል ቢሆንም ነገር ግን ያለ በቂ ምክንያት በጀማዓ መስገድን በመተዉ ወንጀለኛ ይሆናል።
  2. በመስጂድ ውስጥ የሚሰገድ የጀማዓ ሶላት ለብቻ ከሚሰገድ ሶላት በሀያ አምስት ወይም በሀያ ስድስት ወይም በሀያ ሰባት ደረጃ ይበልጣል።
  3. ለአማኞች ዱዓ ማድረግ ከመላእክት የስራ ድርሻዎች መካከል አንዱ ነው።
  4. ዉዱእ አድርጎ መስጂድ መሄድ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ