عَن أَبي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«تَفْضُلُ صَلاَةُ الجَمِيعِ صَلاَةَ أَحَدِكُمْ وَحْدَهُ، بِخَمْسٍ وَعِشْرِينَ جُزْءًا، وَتَجْتَمِعُ مَلاَئِكَةُ اللَّيْلِ وَمَلاَئِكَةُ النَّهَارِ فِي صَلاَةِ الفَجْرِ» ثُمَّ يَقُولُ أَبُو هُرَيْرَةَ: فَاقْرَءُوا إِنْ شِئْتُمْ: {إِنَّ قُرْآنَ الفَجْرِ كَانَ مَشْهُودًا} [الإسراء: 78].
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 648]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
"አንዳችሁ ለብቻው የሚሰግደውን ሶላት የህብረት ሶላት በሃያ አምስት ክፍል (እጥፍ) ይበልጠዋል። የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት ይገናኛሉ።" ቀጥሎም አቡ ሁረይራ እንዲህ አለ: ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ {የጎህ ሶላት ( መላእክት) የሚጣዱት ነውና።} [አልኢስራእ:78]»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 648]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰውዬው ከኢማም ጋር በህብረት የሚሰግደው ሶላት ምንዳና አጅሩ ቤቱ ወይም ሱቁ ውስጥ ብቻውን ከሚሰግደው ሃያ አምስት ሶላት እንደሚበልጥ ገለፁ። ቀጥለው ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የምሽትና የቀን መልዐክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት እንደሚሰባሰቡ አወሱ። ቀጥሎም አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ ይህንን ለማመሳከር እንዲህ አለ:
ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ: {የጎህ ሶላት (መላእክት) የሚጣዱት ነውና።} [አልኢስራእ:78] ማለትም: የፈጅር ሶላት የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች የሚገኙበት ነው ማለት ነው።