عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه:
أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَرَأَ فِي رَكْعَتَيِ الْفَجْرِ: {قُلْ يَا أَيُّهَا الْكَافِرُونَ}، وَ{قُلْ هُوَ اللهُ أَحَدٌ}.
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 726]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው:
"የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በፈጅር ሁለት ረከዓዎች ላይ {ቁል ያ አዩሃል ካፊሩን} እና {ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን አነበቡ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 726]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በፈጅር ሱና ሶላት ላይ ከፋቲሓ ቀጥለው በመጀመሪያው ረከዓ {ቁል ያ አዩሃል ካፊሩን} የ(አልካፊሩን) ምእራፍን በሁለተኛው ረከዓ ደግሞ {ቁል ሁወሏሁ አሐድ} የ(አልኢኽላስ) ምእራፍን መቅራት ይወዱ ነበር።