+ -

عن أَبي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه:
أنه كَانَ يُكَبِّرُ فِي كُلِّ صَلَاةٍ مِنَ الْمَكْتُوبَةِ وَغَيْرِهَا، فِي رَمَضَانَ وَغَيْرِهِ، فَيُكَبِّرُ حِينَ يَقُومُ، ثُمَّ يُكَبِّرُ حِينَ يَرْكَعُ، ثُمَّ يَقُولُ: سَمِعَ اللهُ لِمَنْ حَمِدَهُ، ثُمَّ يَقُولُ: رَبَّنَا وَلَكَ الْحَمْدُ، قَبْلَ أَنْ يَسْجُدَ، ثُمَّ يَقُولُ: اللهُ أَكْبَرُ حِينَ يَهْوِي سَاجِدًا، ثُمَّ يُكَبِّرُ حِينَ يَرْفَعُ رَأْسَهُ مِنَ السُّجُودِ، ثُمَّ يُكَبِّرُ حِينَ يَسْجُدُ، ثُمَّ يُكَبِّرُ حِينَ يَرْفَعُ رَأْسَهُ مِنَ السُّجُودِ، ثُمَّ يُكَبِّرُ حِينَ يَقُومُ مِنَ الْجُلُوسِ فِي الِاثْنَتَيْنِ، وَيَفْعَلُ ذَلِكَ فِي كُلِّ رَكْعَةٍ، حَتَّى يَفْرُغَ مِنَ الصَّلَاةِ، ثُمَّ يَقُولُ حِينَ يَنْصَرِفُ: وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، إِنِّي لَأَقْرَبُكُمْ شَبَهًا بِصَلَاةِ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، إِنْ كَانَتْ هَذِهِ لَصَلَاتَهُ حَتَّى فَارَقَ الدُّنْيَا.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 803]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
አቡ ሁረይራ ግዴታ ሶላቶችም ሆኑ ሱና ሶላቶች በረመዳን ውስጥም ሆነ በሌላ ወቅት በሁሉም ሶላቶች ሲሰግድ ተክቢራ ያደርግ ነበር። በሚቆም ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም ሩኩዕ በሚያደርግ ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" "አላህ ላመሰገነው ሰው ሰሚ ነው።" ይላል፤ ከዚያም ሱጁድ ከመውረዱ በፊትም "ረበና ወለከል ሐምድ" "ጌታችን ላንተ ምስጋና የተገባ ነው።" ይላል፤ ከዚያም ወደ ሱጁድ በሚወርድ ጊዜም "አሏሁ አክበር" ይላል፤ ከዚያም ራሱን ከሱጁድ በሚያነሳ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም መልሶ ወደ ሱጁድ በሚወርድ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም መልሶ ራሱን ከሱጁድ በሚያነሳ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም ከሁለተኛው ረከዐ መቀመጥ በኃላ በሚነሳ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል። ሶላቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ በየሁሉም ረከዐ ይህንን ይፈፅማል። ከዚያም በጨረሰ ጊዜ እንዲህ ይላል: " ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለሁ እኔ ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ጋር ለመመሳሰል እጅግ የቀረበውን ሶላት የምሰግድ ነኝ። ዱንያን እስኪለያዩ ድረስ ይህቺው ነበረች አሰጋገዳቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 803]

ትንታኔ

አቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አሰጋገድ ባህሪ ከፊሉን ተናገሩ። እርሳቸው ወደ ሶላት የቆሙ ጊዜ ተክቢረተል ኢሕራም እንደሚያደርጉ፤ ቀጥለው ወደ ሩኩዕ በሚሸጋገሩ ጊዜ፣ ሱጁድ በሚያደርጉ ጊዜ፣ ከሱጁድ ራሳቸውን በሚያነሱ ጊዜ፣ ሁለተኛውን ሱጁድ በሚወርዱ ጊዜ፣ ከርሱም ራሳቸውን ቀና በሚያደርጉበት ጊዜ፣ ባለሶስት ወይም ባለአራት ረከዓ ሶላት ውስጥ ለመጀመሪያው ተሸሁድ ከተቀመጡ በኋላ ከሁለተኛው ረከዓ ሲነሱም ተክቢራ እንደሚያደርጉ፤ ቀጥለውም ሶላቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ በሁሉም የሶላቱ ክፍል ይህንን ይፈፅሙ እንደነበር ተናገሩ። ወገባቸውን ከሩኩዕ በሚያነሱ ጊዜም "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" ይሉ ነበር። ከዚያም ከቆሙ በኋላ "ረበና ለከል ሐምድ" ይሉ እንደነበርም ተናገሩ።
ከዚያም አቡ ሁረይራ ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ እንዲህ አሉ: ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እኔ የአላህ መልዕክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በማመሳሰል ከናንተ እጅግ የቀረብኩኝ ነኝ። ይህቺን አለም እስከሚለያዩ ድረስም የአሰጋገዳቸው ባህሪ ይህቺው ነበረች።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከሩኩዕ በሚነሱነት ጊዜ ካልሆነ በቀር በየሁሉም መነሳትና መውረድ መካከል ተክቢራ እንደሚደረግ እንረዳለን። ከሩኩዕ ሲነሱ ግን "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" ነው የሚባለው።
  2. ሶሐቦች ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመከተልና ሱናቸውን በመጠበቅ ላይ ያላቸውን ጉጉት እንረዳለን።
ተጨማሪ