የሐዲሦች ዝርዝር
እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ
عربي
الإنجليزية
الأوردية
እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ)
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ምግብ ቀርቦ አልያም ሁለቱ ቆሻሻዎች እያጨናነቁት ሶላት የለም።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የጁሙዐ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሳለ ለባልደረባህ 'ዝም በል!' ካልከው በርግጥም ውድቅ ንግግርን ተናግረሀል።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት
عربي
الإنجليزية
الأوردية
በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የሱብሒን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ከለላ ስር ነው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሁሉም ሶላቶች በኋላ እነዚህን ውዳሴዎች ይሉ ነበር።'
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'
عربي
الإنجليزية
الأوردية
'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'
عربي
الإنجليزية
الأوردية
እነዚህ ከመካከላቸው መልካም (ጻድቅ) ባርያ ወይም መልካም ሰው ሲሞት በመቃብሩ ላይ መስገጃን የሚገነቡና
عربي
الإنجليزية
الأوردية
በሰባት አጥንቶቼ ሱጁድ እንዳደርግ ታዝዣለሁ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል "አላሁመግፊር ሊ ወርሐምኒ ወዓፊኒ ወህዲኒ ወርዙቅኒ" ይሉ ነበር። ትርጉሙም (አላህ ሆይ! ማረኝ፣ እዘንልኝም፣ ጤናን ለግሰኝም፣ ምራኝም፣ ሲሳይን ለግሰኝም) ማለት ነው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም
عربي
الإنجليزية
الأوردية
'ቁመህ ስገድ! ካልቻልክ ተቀምጠህ ስገድ! ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ ስገድ። '
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የሶላትን ጥሪ ትሰማለህን?' አሉት። እርሱም 'አዎን' አላቸው። እሳቸውም 'እንግዲያውስ ለጥሪው መልስ ስጥ!' አሉት።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ
عربي
الإنجليزية
الأوردية
እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ (ከተቀበልኩ) ከቆጠርኩና
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለው በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል
عربي
الإنجليزية
الأوردية
'አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜ አንዳችሁ ከልቡ 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ሶላትን የረሳ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ይስገድ። ከዚህ በቀር ማካካሻ የለውም።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'
عربي
الإنجليزية
الأوردية
'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'
عربي
الإنجليزية
الأوردية
(የአዛንን) ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) እንደሚለው በሉ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት እንዳያደርገው ወይም አላህ የሰውነት ቅርፁን የአህያ የሰውነት ቅርፅ እንዳያደርግበት አይፈራምን?!
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በሚከፍቱበት ወቅትና
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄ በእጃቸው መካከል ሆኖ አንድን የቁርአን ምእራፍ እንደሚያስተምሩኝ ተሸሁድን አስተማሩኝ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አላህ ሆይ! እኔ ከቀብር ቅጣት፣ ከእሳት ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተና እና ከመሲሕ ደጃል ፈተና ባንተው እጠበቃለሁ።'
عربي
الإنجليزية
الأوردية
'አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመግሪብ
عربي
الإنجليزية
الأوردية
በአላህ መንገድ መታገል ነው።' አሉ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን በመመስከር፣ ሶላትን በማቋቋም፣ ዘካን በመስጠት፣ መሪዎችን በመስማትና በመታዘዝ ላይ፣ ለሁሉም ሙስሊም ተቆርቋሪ (ታማኝ/ ቅን) በመሆን ላይ ቃል ኪዳን ተጋቧሃቸው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ከየሁሉም ሶላት መጠናቀቂያ ላይ 'አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ፣ ወሹክሪከ፣ ወሑስኒ ዒባደቲክ' ማለትን እንዳትተው አደራ እልሃለሁ።" አሉኝ።» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።) ማለት ነው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አላሁመ አዑዙ ቢሪዷከ ሚን ሰኸጢክ፣ ወቢሙዓፋቲከ ሚን ዑቁበቲክ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚንክ፣ ላኡሕሲ ሠናአን ዐለይክ አንተ ከማ አሥነይተ ዐላ ነፍሲክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ከቁጣህ በውዴታህ፣ ከቅጣትህ በይቅር ባይነትህ እጠበቃለሁ፤ ከአንተ በአንተ እጠበቃለሁ፤ አንተ እራስህን ያወደስከውን ያህል ላወድስህ አልችልም።" ማለት ነው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋ ድረስ ምሽቱን የተኛ ሰውዬ ተወሳ። እርሳቸውም "ይህ ሸይጧን ጆሮዎቹ ውስጥ ወይም ጆሮው ውስጥ የሸናበት ሰው ነው።" አሉ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ሁለቱን የቀዝቃዛ ወቅቶች ሶላት የሰገደ ሰው ጀነት ገባ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
'ሰውዬው በህብረት የሚሰግደው ሶላት በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው ሶላት ሀያ ምናምን ደረጃ ትበልጣለች።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት የበላ ሰው ከኛ ገለል ይበል ወይም ከመስጂዳችን ገለል ይበል። ቤቱም ይቀመጥ" አሉ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
'ንገሩኝ እስኪ! አንዳችሁ በር ላይ በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት ወንዝ ቢኖር ይህ ከእድፉ ያስቀራል ትላላችሁን?
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደኛ መጡ። እኛም እንዲህ ብለን ጠየቅናቸው የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶ ላይ እንዴት ሰላምታ እንደምናቀርብ አውቀናል። በርሶ ላይ ሶላት የምናወርደውስ እንዴት ነው?
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የመጽሐፉን መክፈቻ (ፋቲሓን) ያላነበበ ሰው ሶላት የለውም።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ከናንተ መካከል ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው ይታጠብ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ዉዱእን አሳምሮ አድርጎ ወደ ጁሙዓ በመምጣት ኹጥባን ዝም ብሎ ያዳመጠ በዚህኛው ጁሙዓና በቀጣዩ ጁሙዓ መካከል የሰራው ተጨማሪም ሶስት ቀን የሰራው ወንጀል ይማራል።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ማለዳ ላይ ወይም ከቀትር በኋላ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ማልዶ በሄደና ከቀትር በኋላ በሄደ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ በሰላም ጀነት ትገባላችሁ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ፀሐይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
'ትልቅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ግዴታ ሶላት አጋጥሞት ዉዱኡን፣ ተመስጦውንና ሩኩዑን አሳምሮ የሚሰግድ አንድም ሙስሊም የለም፤ ከሶላቷ በፊት የነበረበትን ወንጀል ማስማሪያ ቢሆነው እንጂ፤ ይህም እድሜ ልኩን ነው።'
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ አስከትሎ የሚላቸው ወይም የሚተገበራቸው የማይከስርባቸው ቃላት: ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተሕሚድ" (አልሐምዱ ሊላህ)፣ ሰላሳ አራት ጊዜ "ተክቢራ" (አላሁ አክበር) ማለት ናቸው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አዛን ሲባል የሰማ ጊዜ: 'አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ወአነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ ረዲቱ ቢላሂ ረበን ወቢሙሐመደን ረሱለን ወቢል ኢስላሚ ዲና' ያለ ሰው ወንጀሉ ይማራል።" (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የሌለው ነው። ሙሐመድም የአላህ ባሪያውና መልክተኛው ናቸው ብዬ እመሰክራለሁ፤ በአላህ ጌትነት፣ በሙሐመድ መልክተኝነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት ወድጃለሁ።)
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ለአቅመ አዳም በደረሰ ሰው ላይ ሁሉ የጁሙዓ ቀን መታጠብ፣ ጥርሱን ሊፍቅና ካገኘም ሽቶ መቀባቱ ግዴታ ነው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሶስት ወቅቶች ላይ ከመስገድ ወይም ሟቾቻችንን ከመቅበር ይከለክሉን ነበር።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አዛን በሚሰማ ጊዜ ‹አልላሁመ ረበ ሀዚሂ አድደዕወቲ አትታመቲ ወስሰላቲል ቃኢመህ አቲ ሙሐመደኒል ወሲለተ ወልፈዲለተ ወብዐሥሁ መቃመን መሕሙደኒለዚ ወዐድተህ› ያለ ሰው የትንሳኤ ቀን ምልጃዬ ትፀድቅለታለች።" ትርጉሙም "የዚህ የተሟላ ጥሪና የምትቆመው ሶላት ጌታ የሆንከው አላህ ሆይ! ለሙሐመድ ወሲላና ፈዲላን ስጣቸው፤ ቃል የገባህላቸውን ምስጉን ስፍራም ስጣቸው።" ማለት ነው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አንዳችሁ ትከሻዎቹ ላይ አንዳችም ነገር የሌለ ሆኖ በአንድ ልብስ ብቻ አይስገድ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ሰዎች ሶላታቸው ውስጥ ሆነው ዓይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉት ምን ሆነው ነው!?" በዚህ ዙሪያም አጠንክረው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ "ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ ወይም አይናቸው ትነጠቃለች።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ሱጁድ በወረድክ ጊዜ መዳፎችህን መሬት ላይ አኑር! ክንድህንም ከፍ አድርግ!
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ሰገድኩኝ። ወደ ቀኛቸው "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ" በማለት ያሰላምቱ ነበር። ወደ ግራቸው ዞረው ደሞ "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ" ይሉ ነበር።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ከሁሉም (ግዴታ) ሶላት በኋላ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያጠራ (ሱብሓነሏህ) ያለ፤ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያመሰገነ (አልሐምዱ ሊላህ) ያለ፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ተክቢራ (አላሁ አክበር) ያለ፤ ይህም በድምሩ ዘጠና ዘጠኝ ሲሆን መቶ መሙያውንም "ላኢላሃ ኢለላሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ያለ ሰው ወንጀሉ የባህር አረፋ አምሳያ ቢደርስ እንኳ ይማራል።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ከሁሉም ግዴታ ሶላት በኋላ አየተል ኩርሲይን የቀራ ሰው ጀነት ለመግባት ከሞት በቀር ምንም አይከለክለውም።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አንዳችሁ ሶላቱ ውስጥ የተጠራጠረ ጊዜ ሶስት ይሁን አራት ስንት እንደሰገደ ካላወቀ ጥርጣሬውን ይጣልና እርግጠኛ በሆነበት ላይ ይገንባ። ከዛም ከማሰላመቱ በፊት ሁለት ሱጁዶችን ይውረድ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከዝሁር በፊት አራት ረከዓና ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ አይተዉም ነበር።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ከዝሁር በፊት አራት ረከዓዎች ላይና ከዝሁር በኋላ አራት ረከዓዎች ላይ የተጠባበቀ ሰው አላህ እሳትን በርሱ ላይ እርም አድርጎለታል።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በፈጅር ሁለት ረከዓዎች ላይ {ቁል ያ አዩሃል ካፊሩን} እና {ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን አነበቡ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አንዳችሁ ለብቻው የሚሰግደውን ሶላት የህብረት ሶላት በሃያ አምስት ክፍል (እጥፍ) ይበልጠዋል። የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት ይገናኛሉ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ለወንዶች ምርጡ የሶላት ሰልፍ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው። መጥፎው ደግሞ የመጨረሻው ነው። ለሴቶች ምርጡ ሰልፍ የመጨረሻው ሰልፍ ነው። መጥፎው ደግሞ የመጀመሪያው ነው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሰውዬ ከሰልፍ ኋላ ብቻውን ሲሰግድ ተመለከቱትና ሶላቱን እንዲደግመው አዘዙት።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
እነዚህ ሁለት ሶላቶች በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባድ ሶላት ናቸው። በነዚህ ሶላቶች ያለውን ምንዳ ብታውቁ ኖሮ በጉልበታችሁ እየዳኻችሁም ቢሆን ትመጡ ነበር።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ከሶስት ዓይነት አካላት ላይ ብእር ተነስቷል። የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ፤ ህፃን ልጅ አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ እና እብድ ጤነኛ እስኪሆን ድረስ ነው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አዛን ባዩን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ለአላህ ብሎ መስጂድን የገነባ አላህም ለርሱ አምሳያውን ጀነት ውስጥ ይገነባለታል።›' አለ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገዱ አንድ ሺህ ሶላቶች የተሻለ ነው። የተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ ይስገድ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
‹አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ: 'አልላሁምመፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲከ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) ይበል። የወጣ ጊዜም ‘አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል።›
عربي
الإنجليزية
الأوردية
‹ቢላል ሆይ! ሶላትን ኢቃም ብለህ በሶላት እረፍት ስጠን።›'
عربي
الإنجليزية
الأوردية
እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህንን የፈፀምኩት በኔ እንድትከተሉና አሰጋገዴንም እንድታውቁ ነው።'
عربي
الإنجليزية
الأوردية
‹ሶላትን መስገድ የፈለጋችሁ ጊዜ ሰልፋችሁን አስተካክሉ። ከዚያም አንድ ሰው ይምራችሁ። ኢማሙ ተክቢራ ያደረገ ጊዜ እናንተም ተክቢራ አድርጉ!
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለሁ እኔ ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ጋር ለመመሳሰል እጅግ የቀረበውን ሶላት የምሰግድ ነኝ። ዱንያን እስኪለያዩ ድረስ ይህቺው ነበረች አሰጋገዳቸው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
‹ከሚሰርቁ ሰዎች ሁሉ እጅግ መጥፎው ሶላቱን የሚሰርቅ ነው።› እርሱም ‹እንዴት ሶላቱን ይሰርቃታል?› አላቸው። እርሳቸውም ‹ሩኩዑንም ሆነ ሱጁዱን ባለማሟላት።› ብለው መለሱለት።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ
عربي
الإنجليزية
الأوردية
'ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ እንዲህ ይሉ ነበር
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለቱ ሱጁዶች መካከል 'ረቢጝፊርሊ ረቢጝፊርሊ' 'ጌታዬ ሆይ! ማረኝ! ጌታዬ ሆይ! ማረኝ!' ይሉ ነበር።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፈጅር ሁለቱ ረከዓን (ቀብሊያ) ለመስገድ የሚያደርጉትን አይነት መጠባበቅ ለሌላ ሱና ሶላት አድርገው አይጠባበቁም ነበር።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስፍራ መስጂዶች ናቸው። አላህ ዘንድ እጅግ የሚጠላው ስፍራ ገበያዎች ናቸው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
በሰጋጅ ፊት የሚያልፍ ሰው በርሱ ላይ ያለበትን ወንጀል ቢያውቅ ኖሮ በሰጋጅ ፊት ከማለፍ ይልቅ አርባ መቆም ለርሱ መልካም ይሆንለት ነበር።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
እነዚህ መስጂዶች ለዚህ ሽንትና ቆሻሻ አይበጁም። እነዚህ የሚበጁት አላህን ለማውሳት፣ ለሶላትና ቁርአንን ለመቅራት ነው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
አዛን አድራጊዎች የትንሳኤ ቀን ከሰዎች ሁሉ አንገተ ረጃጅሞች ናቸው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የፈጅር አዛን ላይ አዛን ባዩ "ሐይየ ዐለል ፈላሕ" ካለ በኋላ "አስሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም" ማለቱ ከሱና ነው።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ሰዎች በመስጂድ ጉዳይ ሳይፎካከሩ ሰዓቲቱ አትቆምም።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
በየሁሉም ሁለት አዛኖች መካከል ሶላት አለ። በየሁሉም ሁለት አዛኖች መካከል ሶላት አለ።" ቀጥለው በሶስተኛው "ለፈለገ ሰው" አሉ።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ሰዎች ጁመዓዎችን ከመተው ይከልከሉ! አለበለዚያ ግን አላህ በልቦቻቸው ላይ ያሽጋል። ከዚያም ከዝንጉዎች ይሆናሉ።
عربي
الإنجليزية
الإندونيسية
ሶስት ጁመዓዎችን በመሳነፍ የተወ ሰው አላህ ልቡ ላይ ያሽግበታል።
عربي
الإنجليزية
الإندونيسية
ተመለስና ደግመህ ስገድ! አንተ አልሰገድክም።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የቁርአን ምዕራፍ እንደሚያስተምሩን ለጉዳያችን ኢስቲኻራን (አላህን የማማረጥን ዱዓ) እንዴት እንደምናደርግም ያስተምሩን ነበር።
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} [አንነስር:1] የሚለው ምዕራፍ በርሳቸው ላይ ከወረደ በኋላ በሚሰግዱት ሶላት ውስጥ ሁሉ "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ
عربي
الإنجليزية
الأوردية
ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ምንዳ ቢያውቁና እርሱንም እጣ ካልተጣጣሉ በቀር የማያገኙት ቢሆን ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር።
عربي
الإنجليزية
الإندونيسية
ሰባት አካላቶች ከአላህ ጥላ በቀር ጥላ በሌለበት ቀን አላህ በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል።
عربي
الإنجليزية
الإندونيسية
ሶላትን አደራ! በእጆቻችሁ ስር ያሉትን (ባሪያዎችን) አደራ!
عربي
الإنجليزية
الإندونيسية