+ -

عَنْ وَائِل بن حُجرٍ رضي الله عنه قَالَ:
صَلَّيْتُ مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَكَانَ يُسَلِّمُ عَنْ يَمِينِهِ: «السَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ»، وَعَنْ شِمَالِهِ: «السَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللَّهِ».

[حسن] - [رواه أبو داود] - [سنن أبي داود: 997]
المزيــد ...

ከዋኢል ቢን ሑጅር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ሰገድኩኝ። ወደ ቀኛቸው "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ" በማለት ያሰላምቱ ነበር። ወደ ግራቸው ዞረው ደሞ "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ" ይሉ ነበር።»

[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 997]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከሶላታቸው ማጠናቀቅ የፈለጉ ጊዜ ወደ ቀኝና ወደግራቸው ያሰላምቱ ነበር። ይህም "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ" እያሉ በፊታቸው ወደ ቀኝ አቅጣጫ ይዞራሉ። "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላህ" እያሉ ደሞ ወደ ግራ አቅጣጫ ፊታቸውን በማዞር ወደግራ ያሰላምቱ ነበር።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሶላት ውስጥ ሁለት ጊዜ ማሰላመት የተደነገገ ነው። ማሰላመት የሶላቱ ማዕዘንም ነው።
  2. (ወበረካቱህ) የሚለውን ጭማሪ አንዳንዴ ማምጣት ይወደዳል። ምክንያቱም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዚህች ጭማሪ ላይ አልዘወተሩበትምና።
  3. ሶላት ውስጥ ሁለቱን ማሰላመት መናገር ግዴታ የሆነ ማዕዘን ነው። የሰላምታ ቃላቱን እያሉ መዞሩ ግን ተወዳጅ ነው።
  4. "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላህ" የሚባለው እየዞሩ ሳሉ ሊሆን ይገባል። ከርሱ በፊትም አይደለም፤ ከርሱ በኋላም አይደለም።