عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«أَسْوَأُ النَّاسِ سَرَقَةً الَّذِي يَسْرِقُ صَلَاتَهُ» قَالَ: وَكَيْفَ يَسْرِقُ صَلَاتَهُ؟ قال: «لَا يُتِمُّ رُكُوعَهَا، وَلَا سُجُودَهَا».

[صحيح] - [رواه ابن حبان]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
‹ከሚሰርቁ ሰዎች ሁሉ እጅግ መጥፎው ሶላቱን የሚሰርቅ ነው።› እርሱም ‹እንዴት ሶላቱን ይሰርቃታል?› አላቸው። እርሳቸውም ‹ሩኩዑንም ሆነ ሱጁዱን ባለማሟላት።› ብለው መለሱለት።"

Sahih/Authentic. - [Ibn Hibbaan]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በስርቆት እጅግ በጣም መጥፎ ሰው ከሶላቱ የሚሰርቅ ሰው መሆኑን ገለፁ። ይህም ከዚህ ሌባ ተቃራኒ የሌላን ሰው ገንዘብ የወሰደ በዚህች አለም ሊጠቀምበትም ይችል ይሆናል። ይህ ሌባ ግን ከራሱ የምንዳና አጅር ሐቅ የሚሰርቅ ነው። ሶሐቦችም "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እንዴት አንድ ሰው ከሶላቱ ይሰርቃል?" ብለው ጠየቁ። እርሳቸውም "ሩኩዑንም ሆነ ሱጁዱን አያሟላም።" ብለው መለሱ። ይህም በሩኩዑም በሱጁዱም ሲጣደፍ በተሟላ መልኩ እነርሱን አለመፈፀሙ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሶላትን ማሳመር፣ ማእዘናቶቿንም በእርጋታና በተመስጦ መፈፀም አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ሩኩዑም ሱጁዱም የማያሟላ ሰው ከዚህ ተግባሩ ለማራቅና ክልክልነቱን ለማስገንዘብ ሲባል በሌባነት መገለፁን፤
  3. ሶላት ውስጥ ሩኩዕና ሱጁድን መሙላትና እነርሱንም ቀጥ ብሎ መፈፀሙ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።