عَنِ الْبَرَاءِ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِذَا سَجَدْتَ، فَضَعْ كَفَّيْكَ وَارْفَعْ مِرْفَقَيْكَ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 494]
المزيــد ...
ከበራእ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ሱጁድ በወረድክ ጊዜ መዳፎችህን መሬት ላይ አኑር! ክንድህንም ከፍ አድርግ!"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 494]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶላት ውስጥ ሱጁድ ሲወረድ እጆች እንዴት መሆን እንዳለባቸው ገለፁ። ይህም መዳፎቹን መሬት ላይ ማመቻቸትና ጣቶቹ የተጣበቁ ሆነው ወደ ቂብላ አቅጣጫ ማዞር፤ መዳፎቹንም መሬትን ከማስነካትም ከጎኖቹም አራርቆ በማንሳት ነው።