عَنِ ابْنِ أَبِي أَوْفَى رضي الله عنه قَالَ:
كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِذَا رَفَعَ ظَهْرَهُ مِنَ الرُّكُوعِ قَالَ: «سَمِعَ اللهُ لِمَنْ حَمِدَهُ، اللَّهُمَّ رَبَّنَا لَكَ الْحَمْدُ، مِلْءَ السَّمَاوَاتِ وَمِلْءَ الْأَرْضِ وَمِلْءَ مَا شِئْتَ مِنْ شَيْءٍ بَعْدُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 476]
المزيــد ...
ከኢብኑ አቢ አውፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ አላሁመ ረበና ለከል ሐምዱ ሚልአስ-ሰማዋቲ ወልአርድ ወሚልአ ማ ሺእተ ሚን ሸይኢን በዕዱ" ይሉ ነበር። ትርጉሙም "አላህ ላመሰገነው ሰው ሰሚ ነው። አላህ ሆይ! ሰማያትን የሞላ፣ ምድርን የሞላ፣ ከነዚህም በኋላ ያሉ የፈለግከውን ነገሮችን የሞላ ምስጋና ላንተ የተገባ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 476]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ውስጥ ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" ይሉ ነበር። አላህን ያመሰገነ ሰው አላህ ይቀበለዋል፤ ምስጋናውን ተቀብሎ ይመነዳዋል ማለት ነው። ከዚያም "አላሁመ ረበና ለከል ሐምዱ ሚልአስ-ሰማዋቲ ወልአርድ ወሚልአ ማ ሺእተ ሚን ሸይኢን በዕዱ" በሚለው ንግግራቸው ሰማያትን፣ ምድሮችን፣ በመካከላቸው ያለውን፣ አላህ የሻውን ነገርንም ሁሉ በሚሞላ ምስጋና አላህን ያመሰግናል።