عن ابن عباس رضي الله عنهما:
كان النبي صلى الله عليه وسلم يقول بين السجدتين: «اللَّهمَّ اغْفِرْ لي، وارْحَمْنِي، وعافِني، واهْدِني، وارزقْنِي».
[حسن بشواهده] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 850]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል "አላሁመግፊር ሊ ወርሐምኒ ወዓፊኒ ወህዲኒ ወርዙቅኒ" (አላህ ሆይ! ማረኝ፣ እዘንልኝም፣ ጤናን ለግሰኝም፣ ምራኝም፣ ሲሳይን ለግሰኝም) ይሉ ነበር።
[በማመሳከሪያዎቹ ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 850]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሶላታቸው ውስጥ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ሙስሊም የሆነ ሰው በእጅጉ የሚፈልጋቸው ጉዳዮችንና የዱንያንም ሆነ የአኺራን መልካም የሰበሰቡ የሆኑትን: ምህረትን፤ የወንጀል መሸሸግን፤ ይቅር መባልን መፈለግ፤ እዝነቱ እንዲያዳርሰው መፈለግ ፤ ከሚያምታታ፣ ዝንባሌው ከሚገፋፋውና ከበሽታዎችም ጤናማ መሆንን መፈለግ ፤ አላህን ለእውነትና በርሱ ላይ በመፅናት ላይ እንዲመራው መጠየቅ፤ የኢማን፣ የእውቀት ፣ የመልካም ስራ፣ ምርጥና ሐላል የገንዘብ ሲሳይ እንዲለግሰው መለመንን ሁሉ ያጠቃለሉ የሆኑትን እነዚህ አምስት ዱዓዎችን ይለምኑ ነበር።