+ -

عَنْ ‌أَبِي الزُّبَيْرِ قَالَ:
كَانَ ‌ابْنُ الزُّبَيْرِ يَقُولُ فِي دُبُرِ كُلِّ صَلَاةٍ حِينَ يُسَلِّمُ: «لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللهِ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، ‌وَلَا ‌نَعْبُدُ ‌إِلَّا إِيَّاهُ، لَهُ النِّعْمَةُ وَلَهُ الْفَضْلُ وَلَهُ الثَّنَاءُ الْحَسَنُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ» وَقَالَ: «كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يُهَلِّلُ بِهِنَّ دُبُرَ كُلِّ صَلَاةٍ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 594]
المزيــد ...

ከአቡ ዙበይር እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
"ኢብኑ ዙበይር በሁሉም ሶላት ካሰላመተ በኃላ እንዲህ ይሉ ነበር። 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ፤ ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ ፤ ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወላነዕቡዱ ኢላ ኢያህ ለሁ አንኒዕመህ ወለሁልፈዽል ወለሁ አሥሠናኡል ሐሰን፤ ላኢላሃ ኢለሏሁ ሙኽሊሲነ ለሁ ዲነ ወለው ከሪሃል ካፊሩን' አስከትለውም እንዲህ አሉ ' የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሁሉም ሶላቶች በኋላ እነዚህን ውዳሴዎች ይሉ ነበር።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 594]

ትንታኔ

የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሁሉንም ግዴታ ሶላት ካሰላመቱ በኋላ በዚህ ታላቅ ውዳሴ ያወድሱ ነበር። ትርጉሙም:
"ላኢላሃ ኢለሏህ" ማለትም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም።
"ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ" ማለትም አላህ በተመላኪነቱ፣ በጌትነቱ፣ በስሞቹና በባህሪያቶቹ ለሱ ተጋሪ የለውም።
"ለሁል ሙልክ" ማለትም ገደብአልባ ሰፊ ፣ ጠቅላይ ንግስና የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ንግስና ለሱ ነው።
"ወለሁል ሐምድ" ማለትም ልቅ በሆነ ምሉእነት የሚገለፅ ፣ በደስታም ይሁን በችግር ወቅት በማንኛውም ሁኔታ በውዴታና በልቅና ምሉዕ በመሆኑ የሚመሰገን ነው።
"ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ማለትም ችሎታው በሁሉም መልኩ የሞላ አንዳችም የማይሳነው ማንኛውም ጉዳይ ለሱ የማያቅተው ነው።
"ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ" ማለት በአላህ እገዛ ቢሆን እንጂ ከአንድ ሁኔታ ወደ አንድ ሁኔታ መለወጥ የለም፤ አላህን ከመወንጀል እርሱን ወደማምለክ መለወጥም ሀይልም የለም። እርሱ አጋዥ ነውና፤ መመኪያም በርሱ ላይ ነው።
"ላኢላሃ ኢለሏህ ወላነዕቡዱ ኢላ ኢያህ" "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ከርሱ በስተቀርም አናመልክም።" የሚለው የአላህን ተመላኪነትና ሺርክን ውድቅ የማድረግን ሀሳብ የሚያጠናክር ነው። ከርሱ በስተቀርም አምልኮ የሚገባው የለም።
"ለሁ አንኒዕመህ ወለሁል ፈድል" (ፀጋ የርሱ ነው። ችሮታም የርሱ ነው።) እርሱ የፀጋዎች ባለቤትና የሚፈጥር ነው። ለፈለገው ባሮቹም የሚቸረው እሱ ነው።
"ወለሁ አሥሠናኡል ሐሰን" በሁለመናው፣ በባህሪያቶቹ፣ በድርጊቶቹ፣ በፀጋዎቹ ሁሉ መልካም ውዳሴዎች ለርሱ የተገባ ነው።
"ላኢላሃ ኢለሏህ ሙኽሊሲነ ለሁ ዲን" (አምልኮን ለርሱ ያጠራን ስንሆን ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም።) ማለትም በአላህ አምልኮ ያለምንም ይዩልኝና ይስሙልኝ ብቸኛ ያደረግነው ስንሆን ነው የምናመልከው።
"ከሀዲያን ቢጠሉ እንኳ" ማለትም ከሀዲያን ቢጠሉ እንኳ አላህን በመነጠልና በማምለክ ላይ እንፀናለን።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ በዚህ ውዳሴ ላይ መጠባበቅ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  2. አንድ ሙስሊም ከሀዲያን ቢጠሉ እንኳ በእምነቱ ከፍ ያለ ስሜት ሊሰማውና የእምነቱን መገለጫዎች ይፋ ማድረግ ይገባዋል።
  3. ሐዲሥ ውስጥ "ከሶላት በኋላ" የምትለዋ ቃል ስትመጣ ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሰው ውዳሴ ከሆነ ካሰላመተ በኃላ መሆኑ ዱዓእ ከሆነ ደግሞ ሶላት ውስጥ ከማሰላመቱ በፊት መሆኑ መሰረት ነው።
ተጨማሪ