عن أبي هريرة رضي الله عنه: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«لَا تَجْعَلُوا بُيُوتَكُمْ مَقَابِرَ، إِنَّ الشَّيْطَانَ يَنْفِرُ مِنَ الْبَيْتِ الَّذِي تُقْرَأُ فِيهِ سُورَةُ الْبَقَرَةِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 780]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
"ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ። ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ የሚቀራበት ቤትን ይሸሻል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 780]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቶችን ከሶላት አራቁቶ እንደመቃብር የማይሰገድበት ማድረግን ከለከሉ።
በመቀጠልም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ ከሚቀራበት ቤት እንደሚሸሽ ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ቤት ውስጥ ሱና ሶላቶችን የመሰሉ አምልኮዎችን ማብዛት እንደሚወደድ እንረዳለን።
  2. ከጀናዛ ሶላት በስተቀር መቃብር ግቢ ውስጥ ሶላት መስገድ ወደ ሺርክና በተቀባሪው ላይ ወሰን ወደ ማለፍ ከሚያዳርሱ መንገዶች አንዱ ስለሆነ አይፈቀድም።
  3. መቃብር ዘንድ መስገድ መከልከሉ ሶሐቦች ዘንድ የተረጋገጠ ጉዳይ ስለሆነ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቶችን ልክ እንደመቃብር የማይሰገድባቸው ከማድረግ ከለከሉ።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (62)
ተጨማሪ