عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رَضيَ اللهُ عنهُ:
أَنَّ رَجُلًا سَمِعَ رَجُلًا يَقْرَأُ: {قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ} يُرَدِّدُهَا، فَلَمَّا أَصْبَحَ جَاءَ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَذَكَرَ ذَلِكَ لَهُ، وَكَأَنَّ الرَّجُلَ يَتَقَالُّهَا، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ إِنَّهَا لَتَعْدِلُ ثُلُثَ القُرْآنِ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 5013]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
«አንድ ሰውዬ የሆነ ሰው {ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን እየደጋገመ ሲያነብ ሰማ። የነጋም ጊዜ ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመምጣት ነገሩን በሚያቃልል ሁኔታ ይህንን አወሳላቸው። የአላህም መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እርሷ (ቁል ሁወሏሁ አሐድ) የቁርአንን ሲሶ ትስተካከላለች።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5013]
አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት: አንድ ሰውዬ ሌላ ሰው የ{ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን ምዕራፍ ሲያነብ ሰማ። ምሽቱን ሁሉ ሌላ ምዕራፍ ሳይጨምር እርሷን ብቻ ነበር እየደጋገመ የሚያነበው። የነጋም ጊዜ ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመምጣት ይህንን አወሳላቸው። የጠያቂው አነጋገርም ምዕራፏን ያሳነሳት ይመስላል። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አፅንዖት ለመስጠት በመማል "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እርሷ የቁርአንን ሲሶ ትስተካከላለች።" አሉ።