عن أبي مسعود رضي الله عنه قال: قال النبي صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ قَرَأَ بِالْآيَتَيْنِ مِنْ آخِرِ سُورَةِ الْبَقَرَةِ فِي لَيْلَةٍ كَفَتَاهُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5009]
المزيــد ...
ከአቢ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5009]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በምሽት ውስጥ የበቀራህ ምእራፍ የመጨረሻዎቹን ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው አላህ መጥፎና ጎጂ ከሆኑ ነገሮች እንደሚበቃው ተናገሩ። ለሌሊት ሶላት ከመቆም ይበቁታል ማለት ነውም ተብሏል። ሌሎች ውዳሴዎችን ከማለት ይበቁታል ማለት ነውም ተብሏል። ለሌሊት ሶላት የሚቀራ ዝቅተኛው በቂ የቁርአን አንቀፆች ናቸውም ተብሏል። ከዚህም ውጪ ተብሏል። ምንአልባት ሁሉም ከላይ የተጠቀሱትን ትርጓሜዎችን ቃሉ ስለሚሰበስባቸው ሁሉም ትክክለኛ ትርጓሜ ሊሆኑ ይችላሉ።