عن أبي الدرداء رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ رَدَّ عَنْ عِرْضِ أَخِيهِ رَدَّ اللهُ عَنْ وَجْهِهِ النَّارَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ».

[صحيح] - [رواه الترمذي وأحمد]
المزيــد ...

ከአቡ ደርዳእ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።"

Sahih/Authentic. - [At-Tirmidhi]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙስሊም ወንድሙ በራቀ ወቅት እንዳይወገዝ ወይም በርሱ ላይ መጥፎ እንዳይደርስበት በመከልከል ከሙስሊም ወንድሙ ክብር ለተከላከለ ሰው አላህ የትንሳኤ ቀን ቅጣትን ከሱ እንደሚከላከልለት ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሙስሊሞችን ክብር የሚነካ ንግግር መናገር መከልከሉን፤
  2. ምንዳ በስራ አምሳያ (ልክ) ነው። ከወንድሙ ክብር ለተከላከለ ሰው አላህም ከሱ ላይ እሳትን ይከላከልለታል።
  3. ኢስላም በተከታዮቹ መካከል ወንድማማችነትና መረዳዳትን የሚያጠናክር እምነት መሆኑን እንረዳለን።