عن أبي هريرة رضي الله عنه عن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«مَا نَقَصَتْ صَدَقَةٌ مِنْ مَالٍ، وَمَا زَادَ اللهُ عَبْدًا بِعَفْوٍ إِلَّا عِزًّا، وَمَا تَوَاضَعَ أَحَدٌ لِلهِ إِلَّا رَفَعَهُ اللهُ».

[صحيح] - [رواه مسلم]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል:-
"ምፅዋት (ከሰጪው) ገንዘብ ላይ አታጎድልም፤ አላህ ለአንድ ባሪያ ይቅር በማለቱ (ምክንያት) ከልቅና በስተቀር አይጨምርለትም፤ አንድም ሰው ለአላህ ብሎ አይተናነስም አላህ ከፍ ያደረገው ቢሆን እንጂ።"

Sahih/Authentic. - [Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ምፅዋት ከሰጪው ላይ መከራን ትከላከላለች እንጂ ገንዘቡን እንደማታጎድል፤ አላህ ለሰጪው ትልቅ መልካምን እንደሚተካለትና መመፅወቱ ጭማሪ እንጂ ጉድለት እንደማይሆን ገለፁ።
መበቀል ወይም ባለቤቱን መቅጣት እየተቻለም ይቅር ማለት ኃይልና ልቅናን እንጂ አይጨምርም።
አንድም ሰው ማንንም ፈርቶ፣ ለማስመሰልና ከሱ ጥቅም ፈልጎ ሳይሆን ለአላህ ፊት ብሎ አይተናነስምም ዝቅ አይልምም ምንዳው ልቅናና ከፍታ ቢሆን እንጂ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አንዳንድ ሰዎች ከዚህ ተቃራኒ ቢያስቡም መልካምና ስኬት የሚገኘው ሸሪዐን በመተግበርና መልካምን በመፈፀም ነው።