የሐዲሦች ዝርዝር

ምፅዋት (ከሰጪው) ገንዘብ ላይ አታጎድልም፤ አላህ ለአንድ ባሪያ ይቅር በማለቱ (ምክንያት) ከልቅና በስተቀር አይጨምርለትም፤ አንድም ሰው ለአላህ ብሎ አይተናነስም አላህ ከፍ ያደረገው ቢሆን እንጂ።
عربي الإنجليزية الأوردية
አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'
عربي الإنجليزية الأوردية
ባሮች የሚያነጉበት አንድም ቀን የለም ሁለት መልዐክ ወርደው እንዲህ የሚሉበት ቢሆን እንጂ፤ አንደኛቸው: "አላህ ሆይ! ለሰጪ ምትኩን ስጠው!" ሲል ሌላኛቸው ደግሞ "አላህ ሆይ! ለቋጣሪ ጥፋትን ስጠው!" ይላል።
عربي الإنجليزية الأوردية
ከናንተ መካከል በርሱና በአላህ መካከል አስተርጓሚ ሳይኖር አላህ የሚያናግረው ቢሆን እንጂ አንድም ሰው የለም
عربي الإنجليزية الأوردية
የሥራ ዓይነቶች ስድስት ሲሆኑ፤ የሰው ዓይነቶች ደግሞ አራት ናቸው። (የሥራ ዓይነቶች) ሁለቱ (ጀነትና እሳትን) የሚያስከትሉ፣ አምሳያን በአምሳያው የሚያስመነዱ፣ በአስር ተባዝታ የምታስመነዳ መልካም ሥራ፣ በሰባት መቶ ተባዝታ የምታስመነዳ መልካም ሥራ ናቸው።
عربي الإنجليزية الأوردية
የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሰዕድ እናት ሞተች ማንኛው ምፅዋት ነው በላጩ? እርሳቸውም "ውሃ" አሉ። እርሱም ጉድጓድ ቆፈረና "ይህቺ ለሰዕድ እናት ነው።" አለ።
عربي الإنجليزية الأوردية
ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ላደረገ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።
عربي الإنجليزية الأوردية
ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት።
عربي الإنجليزية الأوردية
አላህ ለናንተ የምትመፀውቱበትን ነገር አላደረገላችሁምን? ሁሉም ተስቢሕ (ሱብሓነሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተክቢር (አላሁ አክበር) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተሕሚድ (አልሐምዱሊላህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተህሊል (ላኢላሃ ኢለሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከባሌቤታችሁ ጋር ግንኙነት በመፈፀማችሁ ሶደቃ ይገኛል።" አሉ።
عربي الإنجليزية الأوردية
በአላህ መንገድ ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ባሪያ ነፃ ለማውጣት ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ለሚስኪን ምፅዋት ካደረግከው አንድ ዲናር፤ ለቤተሰቦችህ ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር መካከል ትልቅ ምንዳ የሚያስገኘው ለቤተሰብህ ወጪ ያደረግከው ነው።
عربي الإنجليزية الأوردية