+ -

عَنْ خُرَيْمِ بْنِ فَاتِكٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«الْأَعْمَالُ سِتَّةٌ، وَالنَّاسُ أَرْبَعَةٌ، فَمُوجِبَتَانِ، وَمِثْلٌ بِمِثْلٍ، وَحَسَنَةٌ بِعَشْرِ أَمْثَالِهَا، وَحَسَنَةٌ بِسَبْعِ مِائَةٍ، فَأَمَّا الْمُوجِبَتَانِ: فَمَنْ مَاتَ لَا يُشْرِكُ بِاللهِ شَيْئًا دَخَلَ الْجَنَّةَ، وَمَنْ مَاتَ يُشْرِكُ بِاللهِ شَيْئًا دَخَلَ النَّارَ، وَأَمَّا مِثْلٌ بِمِثْلٍ: فَمَنْ هَمَّ بِحَسَنَةٍ حَتَّى يَشْعُرَهَا قَلْبُهُ، وَيَعْلَمَهَا اللهُ مِنْهُ كُتِبَتْ لَهُ حَسَنَةً، وَمَنْ عَمِلَ سَيِّئَةً، كُتِبَتْ عَلَيْهِ سَيِّئَةً، وَمَنْ عَمِلَ حَسَنَةً فَبِعَشْرِ أَمْثَالِهَا، وَمَنْ أَنْفَقَ نَفَقَةً فِي سَبِيلِ اللهِ فَحَسَنَةٌ بِسَبْعِ مِائَةٍ، وَأَمَّا النَّاسُ، فَمُوَسَّعٌ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا مَقْتُورٌ عَلَيْهِ فِي الْآخِرَةِ، وَمَقْتُورٌ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا مُوَسَّعٌ عَلَيْهِ فِي الْآخِرَةِ، وَمَقْتُورٌ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَمُوَسَّعٌ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ».

[حسن] - [رواه أحمد] - [مسند أحمد: 18900]
المزيــد ...

ኹረይም ቢን ፋቲክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦
"የሥራ ዓይነቶች ስድስት ሲሆኑ፤ የሰው ዓይነቶች ደግሞ አራት ናቸው። (የሥራ ዓይነቶች) ሁለቱ (ጀነትና እሳትን) የሚያስከትሉ፣ አምሳያን በአምሳያው የሚያስመነዱ፣ በአስር ተባዝታ የምታስመነዳ መልካም ሥራ፣ በሰባት መቶ ተባዝታ የምታስመነዳ መልካም ሥራ ናቸው። ሁለቱ (ጀነትና እሳትን) የሚያስከትሉት፥ በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ጀነት ገባ፤ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ደግሞ እሳት ገባ። አምሳያን በአምሳያው የሚያስመነዱ ደግሞ፥ ቀልቡ እንደሚሠራው እስኪሰማውና አላህ የሱን (ቁርጠኝነት) እስኪያውቅለት ድረስ መልካም ስራ ለመሥራት ያሰበ (ከዛም ካልሰራው) አንድ መልካም ሥራ ተብሎ ይጻፍለታል፤ መጥፎ ሥራን የሠራ አንድ መጥፎ ሥራ ተብሎ ይፃፍበታል። አንድ መልካም ሥራን የሠራ ምንዳው በአስር ተባዝቶ ይፃፍለታል። በአላህ መንገድ ላይ አንዲትን ምፅዋት የመፀወተ ምንዳው እስከ ሰባት መቶ ተባዝቶ ይጻፍለታል። የሰዎች ዓይነት ደግሞ ዱንያ ለሱ የሰፋችለት አኺራው ግን የተጣበበበት፣ዱንያ ለሱ የጠበበችበት አኺራ ግን የሰፋችለት፣ ዱንያም አኺራም ለሱ የተጣበቡበት፣ ዱንያም አኺራም ለሱ የሰፉለት ናቸው።

[ሐሰን ነው።] - [አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሙስነድ አሕመድ - 18900]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሥራዎች ስድስት ዓይነት መሆናቸውን ሰዎች ደግሞ አራት አይነት መሆናቸውን ተናገሩ። ስድስቱ የሥራ አይነቶች: -
የመጀመሪያው: በአላህ ላይ አንዳችን ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት ለሱ ፀናችለት።
ሁለተኛ: በአላህ ላይ አንዳችን አካል እያጋራ የሞተ ሰው እሳት በሱ ላይ የፀናችና በውስጧም ዘውታሪ ነው።
እነዚህ ሁለት ሥራዎች እሳትና ጀነትን የሚያፀኑ ናቸው።
ሦስተኛ: የተነየተ መልካም ስራ ነው። ቀልቡ እንደሚሠራው እስኪሰማውና አላህም የኒያውን እውነተኝነት እስኪያውቅለት ድረስ በእውነተኛ ኒያ መልካም ሥራን ለመሥራት የነየተ ከዚያም ይህን የነየተውን መልካም ሥራ መሥራት እንዳይችል የሚያደርግ ጉዳይ የተጋረጠበት ሰው ሙሉ መልካም ሥራ ይጻፍለታል።
አራተኛ: የተሠራች መጥፎ ተግባር ናት። መጥፎን ሥራ የሠራ ሰው አንድ መጥፎ ሥራ እንደሠራ ይጻፍበታል።
ሁለቱ (ሦስተኛውና አራተኛው) ያለምንም ብዜት በሠራው ሥራ አምሳያ የሚያስመነዱ ሥራዎች ናቸው።
አምስተኛ: አምሳያዋ በአስር ተባዝቶ የሚያስመነዳ መልካም ሥራ ነው። እሱም አንድን መልካም ስራ ለመሥራት ነይቶ የሠራ ሰው ለሱ አስር ምንዳ ይጻፍለታል።
ስድስተኛ: በሰባት መቶ እጥፍ ተባዝቶ የሚመነዳ መልካም ሥራ ነው። እሱም አንድን ምፅዋት በአላህ መንገድ የመፀወተ ሰው ይህቺ መልካም ሥራ በሰባት መቶ ተባዝታ ትጻፍለታለች። ይህም ከፍ ያለውና የጠራው አላህ በባሮቹ ላይ የዋለው ችሮታና ቸርነት ነው።
አራቱ የሰው አይነቶች ደግሞ፦
የመጀመሪያው: በዱንያ ውስጥ ሲሳዩ የሰፋለት፣ በውስጧ የሚደሰትና የፈለገውን የሚያገኝ ሲሆን ነገር ግን አኺራ በሱ ላይ የጠበበችና መመለሻው እሳት የሆነ ሀብታም ከሀዲ ነው።
ሁለተኛው: በዱንያ ውስጥ ሲሳዩ የጠበበችበት ሲሆን ነገር ግን አኺራ ለሱ የሰፋችለትና መመለሻው ወደ ጀነት የሆነ ድኻ አማኝ ነው።
ሶስተኛው: ዱንያም ሆነ አኺራ በሱ ላይ የጠበቡበት ድኻ ካፊር ነው።
አራተኛው: ዱንያም ሆነ አኺራ ለሱ የሰፉለት ሀብታም አማኝ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ችሮታ ትልቅ መሆኑንና መልካም ሥራዎቻቸውን እንደሚያባዛ ፤
  2. መጥፎ ሥራችንን ፍትሀዊ በሆነ መልኩ የአንድን መጥፎ ሥራ ምንዳ አንዲት ብቻ አድርጎ መመንዳቱ የአላህ ቸርነትንና ፍትሀዊነት ያሳየናል ፤
  3. በአላህ ማጋራት ትልቅ መሆኑንና እሱን መስራት ከጀነት መከልከል እንደሚያስከትል ፤
  4. በአላህ መንገድ የመመፅወት ትሩፋት መገለፁ ፤
  5. በአላህ መንገድ የመመፅወት ምንዳ የመነባበር መነሻው ከሰባት መቶ እጥፍ ነው። የዚህ ምክንያትም የአላህን ንግግር ከፍ ለማድረግ ስለምታግዝ ነው።
  6. ሰዎች ዓይነታቸው መብራራቱና የተለያዩ መሆናቸውም መገለፁ ፤
  7. ዱንያ ለአማኝም ሆነ ለከሀዲያን የምትዘረጋ ስትሆን አኺራ (ጀነት) ግን ለአማኝ ካልሆነ በቀር አትዘረጋም (አትሰጥም)።