عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنَّ اللهَ لَا يَظْلِمُ مُؤْمِنًا حَسَنَةً، يُعْطَى بِهَا فِي الدُّنْيَا وَيُجْزَى بِهَا فِي الْآخِرَةِ، وَأَمَّا الْكَافِرُ فَيُطْعَمُ بِحَسَنَاتِ مَا عَمِلَ بِهَا لِلَّهِ فِي الدُّنْيَا، حَتَّى إِذَا أَفْضَى إِلَى الْآخِرَةِ، لَمْ تَكُنْ لَهُ حَسَنَةٌ يُجْزَى بِهَا».

[صحيح] - [رواه مسلم]
المزيــد ...

አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦
"አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል። ካፊር ግን ለአላህ ብሎ በሠራው መልካም ሥራ ምክንያት በዱንያ እንዲበላ ይደረጋል። ወደ አኺራ የተሸጋገረ ጊዜ በአኺራ የሚመነዳበት መልካም ሥራ አይኖረውም።"

Sahih/Authentic. - [Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አላህ በአማኞች ላይ የዋለውን ትልቅ ችሮታና ከከሀዲያን ጋር ያለውን ፍትሀዊነት ያብራራሉ። አማኝ የሆነ ሰው የመልካም ሥራው ምንዳ ምንም አትጎድልም። በአኺራ ከሚደለብለት (ከሚከማችለት) ምንዳ በተጨማሪ በዱንያም በአምልኮው ምክንያት መልካምን ይሰጠዋል። ይህ ካልሆነ እንኳ ሁሉም ምንዳው ለሱ አኺራ ላይ ይጠበቅለታል። ካፊር ግን ለሠራው መልካም ሥራ የሚመነዳው በዱንያ አላህ በሚሰጠው መልካም ነገር ነው። ወደ አኺራ የተሸጋገረ ጊዜ ምንም የሚመነዳው ክፍያ አይኖረውም። ምክንያቱም በመልካም ሥራ በሁለቱም ዓለም ለመጠቀም የግድ ባለቤቱ አማኝ መሆን ይጠበቅበታል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በክህደት ላይ የሞተ ሰው ምንም ተግባር አይጠቅመውም።
ተጨማሪ