عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ أَنْظَرَ مُعْسِرًا، أَوْ وَضَعَ لَهُ، أَظَلَّهُ اللهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ تَحْتَ ظِلِّ عَرْشِهِ يَوْمَ لَا ظِلَّ إِلَّا ظِلُّهُ».
[صحيح] - [رواه الترمذي وأحمد] - [سنن الترمذي: 1306]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 1306]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለተበዳሪ የእዳ መክፈያ ጊዜውን ያዘገየለት ወይም ያለበትን እዳ ከሱ ላይ ይቅር ያለ ምንዳው፦ የትንሳኤ ቀን ፀሀይ ወደ ሰዎች አናት ቀርባ ሀሩሯ በነሱ ላይ በሚበረታበት ወቅት አላህ ከዐርሹ ስር እንደሚያስጠልላቸው ተናገሩ። አላህ ያስጠለለው ሰው ካልሆነ በስተቀር አንድም ሰው ጥላ አያገኝም።