+ -

عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ عَمْرِو بْنِ العَاصِ رضي الله عنهما قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنَّ اللهَ سَيُخَلِّصُ رَجُلًا مِنْ أُمَّتِي عَلَى رُءُوسِ الْخَلَائِقِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، فَيَنْشُرُ عَلَيْهِ تِسْعَةً وَتِسْعِينَ سِجِلًّا، كُلُّ سِجِلٍّ مِثْلُ مَدِّ الْبَصَرِ، ثُمَّ يَقُولُ: أَتُنْكِرُ مِنْ هَذَا شَيْئًا؟ أَظَلَمَكَ كَتَبَتِي الْحَافِظُونَ؟ فَيَقُولُ: لَا يَا رَبِّ، فَيَقُولُ: أَفَلَكَ عُذْرٌ؟ فَيَقُولُ: لَا يَا رَبِّ، فَيَقُولُ: بَلَى إِنَّ لَكَ عِنْدَنَا حَسَنَةً، فَإِنَّهُ لَا ظُلْمَ عَلَيْكَ الْيَوْمَ، فَتُخْرَجُ بِطَاقَةٌ فِيهَا: أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَأَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ، فَيَقُولُ: احْضُرْ وَزْنَكَ، فَيَقُولُ: يَا رَبِّ مَا هَذِهِ الْبِطَاقَةُ مَعَ هَذِهِ السِّجِلَّاتِ؟ فَقَالَ: إِنَّكَ لَا تُظْلَمُ، قَالَ: فَتُوضَعُ السِّجِلَّاتُ فِي كِفَّةٍ، وَالْبِطَاقَةُ فِي كِفَّةٍ، فَطَاشَتِ السِّجِلَّاتُ، وَثَقُلَتِ الْبِطَاقَةُ، فَلَا يَثْقُلُ مَعَ اسْمِ اللهِ شَيْءٌ».

[صحيح] - [رواه الترمذي وابن ماجه] - [سنن الترمذي: 2639]
المزيــد ...

ዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች ከኔ ተከታዮች መካከል አንድ ሰው ይመርጣል። በሱ ላይም ዘጠና ዘጠኝ መዝገብ ይዘረጋበታል፤ ሁሉም መዝገብ ዓይን የሚያየውን ርቀት አምሳያ ያካልላል። ከዚያም "ከዚህ ውስጥ አንዳችም ቢሆን (አልሰራሁትም ብለህ) የምታስተባብለው አለን? ስራን ጠባቂ ጸሐፊዎቼ በድለውሀልን? " ብሎ ይጠይቀዋል። "ጌታዬ ሆይ በፍፁም!" ይላል። "ተቀባይነት ያለው ምክንያትስ \ ማስተባብያስ አለህን?" ይለዋል። " ጌታዬ ሆይ በፍፁም!" ይላል። አላህም "እንዴታ! እኛ ዘንድ አንድ መልካም ሥራ አለችህ። እነሆ ዛሬ ባንተ ላይ ምንም በደል የለም።" ይለዋል። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ (ላኢላሀ ኢለ'ላህ ሙሐመዱ ረሱሉላህ) የሚልን ጽሑፍ የያዘች አንድ ካርድ ትወጣለች። አላህ "ሚዛንህ ላይ ተገኝ!" ይለዋል። እሱም "ጌታዬ ሆይ ይህቺ ካርድ ከነዚህ ሁሉ መዝገቦች ጋር (ስትነፃፀር) ምን ዋጋ አላት? " ይላል። አላህም "አንተ አትበደልም።" ይለዋል። መዝገቦቹ በአንድ በኩል ካርዷ በአንድ በኩል ለሚዛን ሲቀመጡ ካርዷ መዝገቦቹን ጠቅልላ ሚዛን ደፋች። ከአላህ ስም ጋር ምንም ሚዛን ሊደፋ አይችልም።

[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2639]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች መካከል ከህዝባቸው አንድ ሰው እንደሚመርጥ ተናገሩ ፤ ሊመረመር ይጠራል፤ በሱ ላይም በዱንያ ይሰራቸው የነበሩትን የወንጀል ተግባራት የያዘ ዘጠና ዘጠኝ መዝገብ ይቀርባል ፤ የእያንዳንዱ መዝገብ ርዝመትም ዓይን የሚያየውን ርቀት ያካልላል። ከዚያም የተከበረውና የላቀው አላህ ለዚህ ሰውዬ፦ "በነዚህ መዝገቦች ውስጥ ከተጻፉት አንድም ብትሆን የምታስተባብለው አለህን?" ይለዋል። "ሥራህን ጸሐፊና ተጠባባቂ የሆኑት መላእክቶቼ በድለውሀልን?" ይለዋል ሰውዬውም "ጌታዬ ሆይ በፍፁም!" ይላል። የተከበረውና የላቀው አላህም "ላንተ በዱንያ አስቀድመህ ለሠራሀቸው ወንጀሎች ተቀባይነት የሚያገኝ ምክንያት አለህን?" በመርሳት፣ በመሳሳት ወይ ባለማወቅ ነው ብለህ ምክንያት የምታቀርብበት ይለዋል። ሰውዬውም፦ "ጌታዬ ሆይ በፍፁም ለኔ ምንም ምክንያት የለኝም።" ይላል። የተከበረውና የላቀው አላህም "እንዴታ! እኛ ዘንድ አንድ መልካም ሥራ አለችህ። እነሆ ዛሬ ባንተ ላይ ምንም በደል የለም" ይላል። ነቢዩ እንዲህ አሉ፦ "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ (አሽሀዱ አን ላኢላሃ ኢለላህ ወ አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉላህ ) የሚል የተፃፈባት አንድ ካርድ ትወጣለች።" የተከበረውና የላቀው አላህ ለዚህ ሰውዬ፦ "ሚዛንህ ላይ ተገኝ!" ይለዋል። ሰውዬውም በመደነቅ "ጌታዬ ሆይ ይህቺ ካርድ ከነዚህ መዝገቦች ጋር (ስትነፃፀር) ምን ትመዝናለች?" ይላል። የተከበረውና የላቀው አላህም፦ "ባንተ ላይ ምንም በደል አይደርስብህም" አለው። ነቢዩ እንዲህ አሉ፦ " መዝገቦቹ በአንድ በኩል ካርዷ በአንድ በኩል ትቀመጣለች። መዝገቦቹ ያሉበት ሚዛን ስትቀል ካርዷ ያለችበት ሚዛን ደግሞ የከበደችና ሚዛን የደፋች ሆነች። በዚህም አላህ ማረው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የተውሒድ ቃል ታላቅነት፥ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ (ሸሀደቱ አላ ኢላሀ ኢለ'ላህ) የሚለው ቃል ሚዛንን የሚከብድ መሆኑን።
  2. ላ ኢላሀ ኢለላህን በምላስ ብቻ መናገር በቂ አይደለም። የግድ ትርጉሙን ማወቅና የሚያስገነዝበውን ተግባር መስራትም አስፈላጊ መሆኑን።
  3. ኢኽላስና የተውሒድ ኃይል ወንጀልን ለማስማር (ለማሰረይ) ምክንያት ናቸው።
  4. ኢማን ቀልቦች ውስጥ በሚኖረው የኢኽላስ መጠን ልክ ይበላለጣል። አንዳንድ ሰው ይህንን የተውሒድ ቃል ቢናገርም ነገር ግን በወንጀሉ ልክ ይቀጣል።