عن جُبَير بن مُطْعِم رضي الله عنه أنه سمع النبي صلى الله عليه وسلم يقول:
«لَا يَدْخُلُ الْجَنَّةَ قَاطِعُ رَحِمٍ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2556]
المزيــد ...

ከጁበይር ቢን ሙጥዒም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እርሱ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማቸው:
"ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2556]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለቅርብ ዘመዶቹ ያለበትን ግዴታ ከመወጣት ይልቅ ዝምድናውን የቆረጠ ሰው ወይም ያወካቸውና ያስከፋቸው ጀነት ላለመግባት የተገባ ነው ብለው ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ዝምድናን መቁረጥ ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።
  2. ዝምድናን መቀጠል በተለምዶ በሚታወቀው መልኩ ነው የሚሆነው። ቦታ፣ ዘመንና ሰዎቹ እንደመለያየታቸው ይለያያል።
  3. ዝምድናን መቀጠል በመዘየር፣ ሶደቃ በመስጠት፣ ለነርሱ በጎ በመዋል፣ ሲታመሙ በመጠየቅ፣ በመልካም በማዘዝ፣ ከመጥፎ በመከልከልና በሌሎችም መልኩ ይፈፀማል።
  4. ዝምድናው የሚቆረጠው ሰው እጅግ ቅርብ ዘመድ በሆነ ቁጥር ወንጀሉም እጅግ የከፋ ይሆናል።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (66)