عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم كان يقول:
«الصَّلَوَاتُ الْخَمْسُ، وَالْجُمُعَةُ إِلَى الْجُمُعَةِ، وَرَمَضَانُ إِلَى رَمَضَانَ، مُكَفِّرَاتٌ مَا بَيْنَهُنَّ إِذَا اجْتَنَبَ الْكَبَائِرَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 233]
المزيــد ...

ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ይሉ ነበር፡
"ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 233]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትላልቆቹን ወንጀሎች መጠንቀቅ እንደቅድመ መስፈርት ከተሟላ አምስቱ በቀንና ሌሊት የሚከናወኑት ሶላቶች፣ በየሳምንቱ የሚሰገደው የጁምዐ ሶላትና በየአመቱ የረመዳንን ወር መፆም በመካከላቸው የሚፈፀምን ትናንሽ ወንጀሎችን እንደሚያስምሩ ነገሩን። ዝሙትና መጠጥን የመሰሉ ከባባድ ወንጀሎች በተውባ ካልሆነ በቀር አይሰረዙም።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከወንጀሎች መካከል ከባባድና ትናንሽ የሚባሉ እንዳሉ እንረዳለን።
  2. ትናንሽ ወንጀሎች የሚሰረዙት ከባባዶቹን ወንጀሎች መራቅን እንደመስፈርት ማሟላት ከተቻለ መሆኑን እንረዳለን።
  3. ትላልቅ ወንጀሎች የሚባሉት ወይ በዱኒያ ቅጣት የተወሰነባቸው፣ ወይም በአኼራ የሚያስከትሉትን የቅጣት አይነት የተነገረባቸው፣ ወይም የአላህ ቁጣ የመጣባቸው፣ ወይም ከባድ ዛቻ ያለባቸው፣ ወይም ደግሞ አድራጊው የተረገመባቸው ሲሆኑ ነው። ለምሳሌ፡ ዝሙት፣ መጠጥ መጠጣት ይጠቀሳሉ።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (67)