عن عائشة رضي الله عنها قالت: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«السِّوَاكُ مَطْهَرَةٌ لِلْفَمِ، مَرْضَاةٌ لِلرَّبِّ».
[صحيح] - [رواه النسائي وأحمد] - [مسند أحمد: 24203]
المزيــد ...
ዓኢሻህ ረዲየሏሁ ዐንሀ እንዲህ ማለቷ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡
'ሲዋክ አፍን የሚያጠራ (የሚያፀዳ)፤ የአሏህንም ውዴታ የሚያስገኝ ነው።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሙስነድ አሕመድ - 24203]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አራክ በተባለው ወይም በአምሳያው በሆነ መፋቂያ ጥርስን መፋቅ አፍን ከቆሻሻ እና ከመጥፎ ጠረን እንደሚያፀዳ ነገሩን። ይህንኑ ማድረግም ለአሏህ ታዛዥነትና ለትእዛዙ ምላሽ መስጠት ከመሆኑ ባሻገር አሏህ የሚወደውን ንፅህናንም የሚያስተርፍ ስለሆነ ድርጊቱ የአሏህን ውዴታ ማግኛ ሰበብ መሆኑን ነገሩን።