+ -

عَنِ شُرَيْحٍ بنِ هانِئٍ قَالَ:
سَأَلْتُ عَائِشَةَ، قُلْتُ: بِأَيِّ شَيْءٍ كَانَ يَبْدَأُ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِذَا دَخَلَ بَيْتَهُ؟ قَالَتْ: بِالسِّوَاكِ.

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 253]
المزيــد ...

ከሹረይሕ ቢን ሃኒእ እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
«እናታችን ዓኢሻን እንዲህ ብየ ጠየቅኳት: "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤታቸው የገቡ ጊዜ በምን ነበር የሚጀምሩት?" እርሷም "በመፋቅ" በማለት መለሰችልኝ።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 253]

ትንታኔ

ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ መካከል በማንኛውም ወቅት በምሽትም ሆነ በቀን ቤታቸው የገቡ ጊዜ በመፋቂያ መጀመር አንዱ ነበር።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በሁሉም ወቅት ባጠቃላይ መፋቂያ መደንገጉን እንረዳለን። ነቢዩ ይወደዳል ባሉበት ወቅት ደሞ ይበልጥ አፅንዖት ይሰጠዋል። ከነርሱም መካከል: ቤት በሚገባ ወቅት፣ ለሶላት በሚቆም ወቅት፣ ዉዱእ በሚደረግበት ወቅት፣ ከእንቅልፍ ከነቁ በኋላና የአፍ ጠረን በሚለወጥበት ወቅት ነው።
  2. ታቢዒዮች እርሳቸውን ለመከተል ብለው ስለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁኔታዎችና ሱናዎች በመጠየቅ ላይ የነበራቸው ጥረት እንረዳለን።
  3. እናታችን ዓኢሻ (ረዺየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤት በሚገቡ ወቅት ስለነበራቸው ሁኔታ መጠየቋ እውቀትን ከባለቤቱና በጉዳዩ እጅግ አዋቂ ከሆነው መውሰድ እንደሚገባ እንረዳለን።
  4. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤት በሚገቡ ወቅት አፋቸውን ማፅዳታቸው ሚስቶቻቸውን በመልካም መኗኗራቸውን ያስረዳናል።