عن عبد الله بن عمرو رضي الله عنهما أن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«بَلِّغُوا عَنِّي وَلَوْ آيَةً، وَحَدِّثُوا عَنْ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَلَا حَرَجَ، وَمَنْ كَذَبَ عَلَيَّ مُتَعَمِّدًا فَلْيَتَبَوَّأْ مَقْعَدَهُ مِنَ النَّارِ».

[صحيح] - [رواه البخاري]
المزيــد ...

ከዓብደሏህ ቢን ዓምር ረዲየሏሁ ዓንሁማ እንደተላለፈው ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡
"ከኔ አንድ አንቀፅም ቢሆን አስተላልፉ። ከቤተ እስራኤላውያንም አውሩ ችግር የለውም። ሆን ብሎ በኔ ላይ የዋሸ መቀመጫውን ከእሳት ያመቻች።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari]

ትንታኔ

ነቢዩ ﷺ ከሳቸው የተማርነውን ቁርአናዊም ይሁን ሓዲሣዊ እውቀት አንድ አንቀፅ ያህል ትንሽ እንኳ ቢሆን እንድናስተላልፈው አዘዙን፤ ይህም ግን የምንጣራበትንና የምናደርሰውን መልእክት ተረድተነው መሆኑ ቅድመ መስፈርቱ ነው። ከዚያም ሽሪዓችን ጋር እስካልተጋጨ ድረስ ከበኒ ኢስራኢሎች የተከሰተባቸውን ክስተትና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ ማውራታችንም ችግር እንደሌለው ገለፁ። ከዚያም በሳቸው ላይ መቅጠፍን አስጠነቀቁ፤ ሆን ብሎ በሳቸው ላይ የዋሸም ጀሀነም ውስጥ ማረፊያውን እንዲይዝ አሳሰቡ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የአሏህን ሸሪዓ ማስተላለፍ እንደሚበረታታና ማንኛውም ሰው ሸምድዶ የተረዳውን ትንሽም ቢሆን ማድረስ እንዳለበት፤
  2. አሏህን በትክክል ለማምለክና መልዕክቱንም ለማድረስ እንዲያስችል ሸሪዓዊ እውቀትን መፈለግ ግዴታ መሆኑን፤
  3. ይህ ከባድ ዛቻ ከሚመለከታቸው ሰዎች ላለመሆን ሲባል የትኛውንም ሓዲሥ ከማስተላለፋችንና ከማሰራጨታችን በፊት በትክክል ከሳቸው መሆኑን ማረጋገጥ ግዴታ እንደሆነ፤
  4. ውሸት ላይ ላለማረፍ ሲባል በተለይም በአሏህ ሸሪዓ ላይ በንግግራችን እውነተኞችና የምናወራውም የተሟላ መረጃው ያለንን ጉዳይ መሆኑ እንደሚበረታታ እንረዳለን።