عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ كَذَبَ عَلَيَّ مُتَعَمِّدًا فَلْيَتَبَوَّأْ مَقْعَدَهُ مِنَ النَّارِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 110]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ሆነ ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ሰው ከእሳት የሆነ መቀመጫውን ያዘጋጅ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 110]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሆን ብሎ ንግግርን ወይም ድርጊትን ወደርሳቸው አስጠግቶ በርሳቸው ላይ የዋሸ ሰው በመጨረሻው ዓለም በርሳቸው ላይ ለመዋሸቱ ምንዳ የእሳት መቀመጫ እንዳለው ገለፁ።