عن أبي أيوب الأنصاري رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«لَا يَحِلُّ لِرَجُلٍ أَنْ يَهْجُرَ أَخَاهُ فَوْقَ ثَلَاثِ لَيَالٍ، يَلْتَقِيَانِ، فَيُعْرِضُ هَذَا وَيُعْرِضُ هَذَا، وَخَيْرُهُمَا الَّذِي يَبْدَأُ بِالسَّلَامِ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከአቡ አዩብ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"ሲገናኙ ይህም እየዞረ ያኛውም እየዞረ ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ከሁለቱ ምርጡ በሰላምታ የሚጀምረው ነው።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ሙስሊም ሙስሊም ወንድሙን አንዱ ሌላኛውን በሚያገኘው ጊዜ ሰላምታም ሳይሰጠውና ሳያናግረው ከሶስት ሌሊቶች በላይ ማኩረፍን ከለከሉ።
ከነዚህ ሁለት ጠበኞች መካከል በላጩ ኩርፊያውን ለማስወገድ የሚሞክርና ሰላምታ የሚጀምረው ነው። እዚህ ሐዲስ ውስጥ ኩርፊያ በማለት የተፈለገው በነፍሱ ፍላጎቶች ያኮረፈ እንደሁ ነው። ወንጀለኞችን፣ የቢድዓ ባለቤቶችንና መጥፎ ጓደኞችን የመሰሉ ሰዎችን ለአላህ ሀቅ ብሎ ማኩረፍ ከሆነ ግን በወቅት ሳይሆን የሚገደበው ኩርፊያው በሚያመጣው ጥቅምና ያለባቸው ችግር በመወገዱ ላይ ነው የሚገደበው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሰውን ልጅ ተፈጥሮ ለመጠበቅ ሲባል ለሶስት ቀንና ከዛ በታች ማኩረፍ እንደተፈቀደ እንረዳለን። ለሶስት ቀናት ማኩረፉም ይቅር የተባለው ይህንኑ ተፈጥሯዊ ባህሪ ለማስተናገድ ሲባል ነው።
  2. ሰላምታ ነፍሶች ውስጥ ያለን አለመግባባት ማስወገዱና የመዋደድ ምልክትም በመሆኑ የሰላምታን ደረጃ ያስረዳናል ፤
  3. ኢስላም በወንድማማችነት ላይና በአማኞቹ አንድነት ዙሪያ መጓጓቱን እንረዳለን።