የሐዲሦች ዝርዝር

አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ላይ አምስት መብቶች አሉት፤ ሰላምታ መመለስ፣ ህመምተኛ መጠየቅ፣ ጀናዛን መሸኘት፣ ጥሪውን መቀበልና ባስነጠሰው ጊዜ 'የርሐሙከሏህ' ማለት ናቸው።'
عربي الإنجليزية الأوردية
ለአንድ ሰው ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ሲገናኙ ይህም ይዞራል ያኛውም ይዞራል። ከሁለቱ ምርጡ ሰላምታ የሚጀምረው ነው።
عربي الإنجليزية الأوردية
አንዳችሁ ወንድሙን ያገኘ ጊዜ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ! በመካከላቸው ዛፍ ወይም ግድግዳ ወይም ድንጋይ ከጋረዳቸው ከዚያም ድጋሚ ቢያገኘው በድጋሚ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ።
عربي الإنجليزية الأوردية
የሚጋልብ ሰው ለእግረኛ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ ለተቀማጭ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'
عربي الإنجليزية الأوردية
አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን በሰላምታ አትጀምሯቸው። ከመካከላቸው አንዱን መንገድ ላይ ባገኛችሁ ጊዜም ወደ ጠባቡ መንገድ አጣብቡት።
عربي الإنجليزية الأوردية
አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።
عربي الإنجليزية الأوردية
አንዳችሁ ወደ መቀመጫ ስፍራ የደረሰ ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ፤ ከመቀመጫ ስፍራ መነሳት የፈለገም ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ። መጀመሪያ ያቀረበው ሰላምታ መጨረሻ ላይ ከሚያቀርበው ሰላምታ የበለጠ አይደለም።
عربي الإنجليزية الأوردية
አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመምጣት "አስሰላሙ ዐለይኩም" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። ቀጥሎም ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "አስር" አሉ።
عربي الإنجليزية الأوردية
ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።
عربي الإنجليزية الأوردية