+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِذَا لَقِيَ أَحَدُكُمْ أَخَاهُ فَلْيُسَلِّمْ عَلَيْهِ، فَإِنْ حَالَتْ بَيْنَهُمَا شَجَرَةٌ أَوْ جِدَارٌ أَوْ حَجَرٌ ثُمَّ لَقِيَهُ فَلْيُسَلِّمْ عَلَيْهِ أَيْضًا».

[صحيح] - [رواه أبو داود] - [سنن أبي داود: 5200]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"አንዳችሁ ወንድሙን ያገኘ ጊዜ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ! በመካከላቸው ዛፍ ወይም ግድግዳ ወይም ድንጋይ ከጋረዳቸው በኃላም ድጋሚ ቢያገኘው በድጋሚ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 5200]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙስሊም ሙስሊም ወንድሙን ባገኘው ጊዜ በርሱ ላይ ሰላምታን ማቅረብ እንደሚገባ አነሳሱ። አንድ ላይ እየተጓዙ እንኳ በመካከላቸው እንደዛፍ ወይም ግድግዳ ወይም ትልቅ ድንጋይ ከለያያቸው በኋላ በድጋሚ ቢያገኘው በርሱ ላይ ሰላምታን እንዲያቀርብ አነሳሱ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሰላምታን ማብዛትና ሁኔታዎች በተለዋወጡ ቁጥር ሰላምታን መደጋገም እንደሚወደድ እንረዳለን።
  2. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሰላምታ ሱናን በማስፋፋትና በዚህም ላይ እንድንበረታ ያላቸውን ከፍተኛ ጥረት እናያለን። ይህም በሙስሊሞች መካከል መተሳሰርንና ውዴታን ስለሚያመጣ ነው።
  3. ሰላምታ የተባለው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ የሚደረገው መጨባበጥ ሳይሆን (አስሰላሙ ዐለይኩም) ወይም (አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ) መባባልን ነው።
  4. ሰላምታ ዱዓ ነው። ሙስሊሞች ቢደጋገም ራሱ ከፊሉ ለከፊሉ ዱዓ መደራረግ ያስፈልጋቸዋል።