عن عائشة رضي الله عنها عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«إِنَّ أَبْغَضَ الرِّجَالِ إِلَى اللهِ الْأَلَدُّ الْخَصِمُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2457]
المزيــد ...
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"ከሰዎች ሁሉ አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላው ደረቅ ተከራካሪ የሆነ ሰው ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2457]
የጠራውና ከፍ ያለው አላህ ከሰዎች ውስጥ ለእውነት እጅ መስጠትን የማይቀበል፣ እውነታውን በክርክሩ ለመመለስ የሚሞክር ወይም እውነትን ይዞ ቢከራከርም ነገር ግን ከሚዛናዊነት በሚያስወጣው መልኩ ክርክርን የሚያበዛና ያለ እውቀት የሚከራከርን ደረቅ ተከራካሪንና ክርክር የሚያበዛን እንደሚጠላ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።