عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه:
أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ يَقُولُ فِي سُجُودِهِ: «اللهُمَّ اغْفِرْ لِي ذَنْبِي كُلَّهُ دِقَّهُ، وَجِلَّهُ، وَأَوَّلَهُ وَآخِرَهُ وَعَلَانِيَتَهُ وَسِرَّهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 483]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሱጁድ ውስጥ እንዲህ ይሉ ነበር "አላሁመግፊርሊ ዘንቢ ኩለሁ ዲቀሁ ወጂለሁ፣ ወአወለሁ ወአኺረሁ፣ ወዐላኒየተሁ ወሲረሁ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ደቂቁንም ትልቁንም፣ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም፣ ግልፁንም፣ ድብቁንም ወንጀሌን ሁሉንም ማረኝ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 483]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሱጁዳቸው ወቅት እንዲህ እያሉ ዱዓእ ያደርጉ ነበር: "አላህ ሆይ ወንጀሌን ማረኝ" በመሸሸጊያህ ሸሽገኝ፤ ተከትሎት የሚመጣውን መከራንም ጠብቀኝ፤ ይቅር በለኝ፤ እለፈኝ (ሁሉንም) ማለትም (ደቂቁንም) ትንሹንም ጥቃቅኑንም፤ (ትልቁንም) ግዙፉንም ብዙውንም፤ (የመጀመሪያውንም) የመጀመሪያውን ወንጀሌንም፤ (የመጨረሻውንም) በነርሱ መካከል ያለውን ወንጀሌንም (ግልፁንም ድብቁንም) ከአንተ በቀር ማንም የማያውቀውን ወንጀሌንም ማረኝ።