عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤْمنين رَضيَ اللهُ عنها قَالَتْ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«يُحْشَرُ النَّاسُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ حُفَاةً عُرَاةً غُرْلًا» قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ النِّسَاءُ وَالرِّجَالُ جَمِيعًا يَنْظُرُ بَعْضُهُمْ إِلَى بَعْضٍ؟ قَالَ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «يَا عَائِشَةُ، الْأَمْرُ أَشَدُّ مِنْ أَنْ يَنْظُرَ بَعْضُهُمْ إِلَى بَعْضٍ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2859]
المزيــد ...
ከአማኞች እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: «የአላህ መልክተኛን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
"ሰዎች የትንሳኤ ቀን ባዶ እግራቸውን፣ ራቁትና ያልተገረዙ ሆነው ይሰበሰባሉ።" እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ወንዶችም ሴቶችም ባጠቃላይ ከፊሉ ወደ ከፊሉ እየተመለከተ?" አልኳቸው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ዓኢሻህ ሆይ! ጉዳዩኮ ከፊሉ ወደ ከፊሉ ከመመልከትም በላይ በጣም ከባድ ነው።" አሉኝ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2859]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የትንሳኤ ቀን የሚከሰተውን አንድ ክስተት እንዲህ በማለት ገለፁ። ሰዎች ለሒሳብ ከቀብራቸው ከተቀሰቀሱ በኋላ ያለ ጫማ በባዶ እግራቸው፣ ያለልብስ ሰውነታቸው ተራቁቶና እናታቸው እንደወለደቻቸው ቀን ያልተገረዙ ሆነው ይሰበሰባሉ። ይህንንም የአማኞች እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- ስትሰማ ተደንቃ እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ወንዶችም ሴቶችም ባጠቃላይ ከፊሉ ወደ ከፊሉ እየተመለከተ?" ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከሞት መቀስቀስ በኋላ የመሰብሰብና የመቆም ጉዳይ ሀፍረተ ገላን ከመመልከትም በላይ የሰዎችን ሃሳብና አይን የሚሰልብ አስደንጋጭነት እንዳለው ገለፁ።