عَنْ عُبَادَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ شَهِدَ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ، وَأَنَّ عِيسَى عَبْدُ اللهِ وَرَسُولُهُ وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَى مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِنْهُ، وَالْجَنَّةُ حَقٌّ، وَالنَّارُ حَقٌّ، أَدْخَلَهُ اللهُ الْجَنَّةَ عَلَى مَا كَانَ مِنَ الْعَمَلِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3435]
المزيــد ...
ከዑባዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ፤ ብቸኛና አጋርም እንደሌለው፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛው መሆናቸውን፤ ዒሳም የአላህ ባሪያና መልክተኛው፣ ወደመርየምም ያስተላለፈው ቃሉና ከርሱ የሆነ መንፈስ መሆኑን፣ ጀነትም እውነት መሆኗን፣ እሳትም እውነት መሆኗን የመሰከረ ሰው በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3435]
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እየነገሩን ያለው: የተውሒድን ቃል ትርጉሙን አውቆ የሚያስፈርደውንም በመስራት የተናገረ ሰው፤ እንዲሁም በሙሐመድም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባርነትና መልክተኝነት የመሰከረ፤ የዒሳን ባርነትና መልክተኝነት ያመነ፤ አላህ ዒሳን "ሁን" በሚለው ቃሉ እንደፈጠራቸውና አላህ ከፈጠራቸው ነፍሶች መካከል አንዱ ነፍስ እንደሆኑም የመሰከረ፤ አይሁዶች ወደርሷ ካስጠጉት ዘለፋም እናቱን መርየምን ያጠራ፤ መኖራቸውንና የአላህ ፀጋና ቅጣቱ መሆናቸውን ከማመን ጋር ጀነትም እውነት መሆኑን፣ እሳትም እውነት መሆናቸውን ያመነ ሰው በአምልኮዎች ላይ ያጓደለና ወንጀሎችም ያሉበት ቢሆን እንኳ በዚህ እምነት ላይ ከሞተ መመለሻው ወደ ጀነት ነው።