عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّهُ قَالَ:
قِيلَ: يَا رَسُولَ اللهِ، مَنْ أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِكَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ؟ قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَقَدْ ظَنَنْتُ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ أَنْ لَا يَسْأَلَنِي عَنْ هَذَا الْحَدِيثِ أَحَدٌ أَوَّلُ مِنْكَ؛ لِمَا رَأَيْتُ مِنْ حِرْصِكَ عَلَى الْحَدِيثِ، أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ، مَنْ قَالَ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ أَوْ نَفْسِهِ»».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 99]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተለለፈው እንዲህ ብለዋል:
"የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የቂያማ ቀን በርሶ ምልጃ ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛው ማን ነው?" ተባሉ። የአላህ መልክተኛም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፡- 'አቡ ሁረይራ ሆይ! ባንተ ላይ ካየሁት የሐዲሥ ጉጉት አንፃር ይህንን ጥያቄ ለመጠየቅ የሚቀድምህ አይኖርም ብዬ አስቤ ነበር። የቂያማ ቀን በኔ አማላጅነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛ የሚሆኑት ጥርት ባለ መልኩ ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት ናቸው።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 99]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የትንሳኤ ቀን በምልጃቸው ከሰዎች ሁሉ የበለጠ እድለኛ የሚሆኑት "ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት" ማለትም ከአሏህ በቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው እንደሌለ አምነው ከሽርክ ይሁን ከይዩልኝና ይስሙልኝም ጥርት ያሉት መሆናቸውን ተናገሩ።